ቻምፒየንስ ሊግ ፡ ዜዝኮ ዩናይትድ ማሜሎዲ ሰንዳውንስን ያስተናግዳል

 የአፍሪካ እግርኳስ | 07-01-2009 

የኦሬንጅ ቻምፒዮንስ ሊግ የግማሽ ፍፃሜ ጨዋታ ዛሬም ሲቀጥል በሰሜን ዛምቢያ የምትገኘው ንዶላ ላይ ዜስኮ ዩናይትድ የደቡብ አፍሪካውን ማሜሎዲ ሰንዳውንስን ያስተናግዳል፡፡

ዜስኮ ከዘጠኝ ቀናት በፊት በዛምቢያ ፕሪምየር ሊግ ጨዋታ ፎረስት ሬንጀርስን 1-0 ያሸነፈ ሲሆን ከሊግ መሪው ዛናኮ በ15 ነጥቦች አንሶ አራተኛ ነው፡፡ ዜስኮ ቀሪ አምስት የሊግ ጨዋታዎች በእጁ የሚገኝ ሲሆን በምድብ አንድ ዋይዳካዛብላንካን ተከትሎ በሁለተኝነት ወደ ግማሽ ፍፃሜው ማለፍ ችሏል፡፡

ማሜሎዲ ሰንዳውን አብሳ ፕሪምየርሺፕ ክብሩን ለማስጠበቅ የሊግ ውድድርን የጀመረ ሲሆን የጨዋታ መደራረብ አሰልጣኝ ፔትሶ ሞሴሜኔን አላስደሰተም፡፡

በዘንድሮው ቻምፒየንስ ሊግ የውድድር ዘመን ዜስኮ በመዳብ ማዕድን ክምችቷ በምትታወቀው ንዶላ ላይ ሽንፈትን አልቀመሰም፡፡ ዜስኮን በሜዳው ማሸነፍ በጣም ፈታኝ ሲሆን በአንፃሩ ደግሞ ብራዚሎቹ ወደ ቻምፒየንስ ሊጉን ግማሽ ፍፃሜ አስቀድመው ማለፍ ችለዋል፡፡ አሰልጣኝ ሞሴሜኔ ለንዶላው ፈተና በዚምባቡዌው አማካይ ካማ ቢላት እና ኪገን ዶሊ ላይ ከፍተኛ ዕምነትን ጥለዋል፡፡ ከዛምቢያ ብሄራዊ ቡድን አሰልጣኝነታቸው በቅርቡ የተነሱት ጆርጅ ላዋንዲማና ደግሞ በኬንያዊው ኢንተርናሽናል ጄሲ ዌሬ ላይ ጥገኛ ይሆናሉ፡፡

ከኦርላንዶ ፓይሬትስ ውጪ አንድም የደቡብ አፍሪካ ክለብ የቻምፒየንስ ሊጉን ክብር አግኝቶ የማያውቅ እንደመሆኑ ሰንዳውንስን ለአዲስ ታሪክ ያነሳሳል ተብሏል፡፡

ጨዋታውን ማዳጋስካራዊው ሃምዳ ናምፒአንደራዛ በመሃል ዳኝነት ሲመራው ረዳቶቹ ጀርሰን ዶስ ሳንቶስ ከአንጎላ እና ቴዮጊኒ ናጂጂማና ከሩዋንዳ ሁነዋል፡፡

ትላንት በተደረገው ሌላ የቻምፒየንስ ሊግ ግማሽ ፍጻሜ ጨዋታ አሌክሳንድሪያ ላይ ዛማሌክ የሞሮኮው ዋይዳድ ክለብ አትሌቲክን 4-0 በመርታት ወደ ፍጻሜው የሚያደርገውን ጉዞ አሳምሯል፡፡

የዛሬ ጨዋታ

15፡30 – ዜስኮ ዩናይትድ (ዛምቢያ) ከ ማሜሎዲ ሰንዳውንስ (ደቡብ አፍሪካ) (ሌቪ ማዋናዋሳ ስታዲየም)

Leave a Reply