ደደቢት ጋናዊ አጥቂ አስፈረመ

በአፍሪካ ቻምፒዮንስ ሊግ የቅድመ ማጣርያ የመጀመርያ ጨዋታውን እሁድ ከዛንዚባሩ ኬኤምኬኤም

ጋር የሚያደርገው ደደቢት ለውድድሩ እንዲረዳው ጋናዊውን የ24 አመት አጥቂ ሳሙኤል ጋንሳህን ከቱኒዝያው ኤ ኤስ ካስሪኔ አስፈርሟል፡፡

ደደቢት የጌታነህ ከበደን መውጣት ተከትሎ ሚካኤል ጆርጅ እና አሸናፊ አደምን ከሲዳማ ቡና ቢያዘዋውርም የአጥቂ መስመሩ ሳስቶ ታይቷል፡፡ጋንሳህ የቱንዚያውን ክለብ ከመቀላቀሉ በፊት በጋና ፕሪሚየር ሊግ ክለቦች የመጫወት ልምድ ያለው መሆኑ ለሰማያዊው ጦር የአፍሪካ ጉዞ ጥሩ ግልጋሎት ያበረክታል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

ጋንሳህ በቻምፒዮንስ ሊጉ የደደቢት ስብስብ ውስጥ የተካተተ ሲሆን እሁድ የመጀመርያ ጨዋታውን ያደርጋል ተብሎ ይጠበቃል፡፡ አጥቂው በደደቢት ውስጥ ከተከላካዩ አዳሙ መሃመድ እና አማካዩ ጋብሬል ሻይቡ በመቀጠል 3ኛው ጋናዊ ተጫዋች ሆኗል፡

{jcomments on}