የወጣቶች እግርኳስ | 07-01-2009
የኢትዮጵያ ከ17 አመት በታች ብሄራዊ ቡድን በአፍሪካ ከ17 አመት በታች ዋንጫ ማጣርያ የመጨረሻ ዙር ነገ ማሊን ይገጥማል፡፡ አርብ ወደ ማሊ ያቀናው ብሄራዊ ቡድን ከነገው ጨዋታ በፊት ዛሬ የመጨረሻ ልምምዱን አከናውኗል፡፡
ከ17 አመት በታች ቡድኑ ትላንት ጠዋት ወደ ማሊ ይበራል ተብሉ ሲጠበቅ በአውሮፕላን መዘግየት ምክንያት አርፍዶ ማምሻውን ማሊ የደረሰ ሲሆን ምሽቱን ቀለል ያለ ልምምድ ሰርቷል፡፡ በዛሬው እለት ደግሞ ነገ በሚጫወትበት ሜዳ የመጨረሻ ልምምቸውን አከናውነዋል፡፡
ቡድናቸችን የMRI የምርመራ ውጤት በፍጥነት ወደ CAF ባለመድረሱ ምክንያት 20 ተጨዋቾችን ይዞ መጓዝ ሲገባው 17 ተጨዋቾችን ብቻ ይዞ ለመጓዝ የተገደደ ሲሆን ከ17ቱ ተጫዋቾች መካከል 3 ግብ ጠባቂዎችን ይዞ መጓዙ አስገራሚ ሆኗል፡፡ አዳዲስ ተካተው በካፍ ያልተረጋገጡት ተጫዋቾች ለመልሱ ጨዋታ ይደርሳሉ ተብሏል፡፡
በማሊ እና ኢትዮጵያ መካከል የሚካሄደው ጨዋታ በባማኮ ማዲቦ ኬይታ ስታዲየም በሃገራችን ሰአት አቆጣጠር ምሽት 1:30 ላይ ይደረጋል፡፡