የኢትዮጵያ ከ17 አመት በታች ብሄራዊ ቡድን በማሊ 2-0 ተረቷል

 የወጣቶች እግርኳስ | 08-01-2009 

በአፍሪካ ከ17 አመት በታች ዋንጫ ማጣርያ የመጨረሻ ዙር ባማኮ ማዲቦ ኬይታ ስታዲየም ላይ ማሊ ኢትዮጵያን 2-0 ረታለች፡፡

በኢትዮጵያ ሰአት አቆጣጠር ምሽት 1:30 ላይ የተጀመረው የሁለቱ ቡድኖች ጨዋታ በመጀመርያው አጋማሽ ግብ ያላስተናገደ ሲሆን ማሊዎች ኢላማውን የጠበቀ ሙከራ ማድረግ የቻሉት አንድ ጊዜ ብቻ ነበር፡፡

ጨዋታው ግብ ለማስተናገድ ረጅም ደቂቃዎች ሲወስድ በ72ኛው ደቂቃ በኢትዮጵያ የግብ ክልል በተሰራ ጥፋት የተገኘውን የፍጹም ቅጣት ምት ሀጂ ድራሜ ወደ ግብነት ቀይሮ ማሊን ቀዳሚ አድርጓል፡፡ በ86ኛው ደቂቃ ደግሞ ድጄሞሳ ትራኦሬ የማሊን መሪነት ወደ ሁለት ከፍ አድርጎ ጨዋታው በማሊ 2-0 አሸናፊነት ተጠናቋል፡፡

የሁለቱ ቡድኖች የመልስ ጨዋታ ከሁለት ሳምንት በኋላ ኢትዮጵያ ላይ ይካሄዳል፡፡ ኢትዮጵያ ከማሊው ጨዋታ በፊት ዝግጅቷን በሀዋሳ እንደማድረጓ እና የአዲስ ከበባ ስታድየም በሜዳ ጥገና ላይ እንደመሆኑ ጨዋታው ሀዋሳ ላይ ሊካሄድ ይችላል፡፡

picsart_1474231283634

Leave a Reply