ካሜሮን 2016፡ የአፍሪካ ሴቶች ዋንጫ የምድብ ድልድል ይፋ ሆኗል

 የሴቶች እግርኳስ | 09-01-2009 

በካሜሮን አዘጋጅነት ህዳር 10 የሚጀመረው የአፍሪካ ሴቶች ዋንጫ የምድብ ድልድል ትላንት ያውንዴ ላይ ይፋ ሆኗል፡፡ በየሁለት ዓመት ልዩነት የሚደረገው ውድድርን በ2014 ያዘጋጀችው ናሚቢያ ስትሆን በዘንድሮው ውድድር አዘጋጇን ካሜሮንን ጨምሮ ሰባት ሃገራት በሁለት ምድብ ተከፍለው ጨዋታቸውን ያካሂዳሉ፡፡

የካፍ ፕሬዝደንት ኢሳ ሃያቱ እና የካሜሮን እግርኳስ ፌደሬሽን ፕሬዝደንት ቶምቢ አሮኮ ሲዲኪ እንዲሁም የቀድሞ የካሜሮን ዝነኞች ሪጎቤር ሶንግ እና ሮጀር ሚላ በተገኙበት የምድብ ድልድሉ የተካሄደ ሲሆን የምስራቅ አፍሪካ ብቸኛዋ ተወካይ ኬንያ በምድብ ሁለት ከሃያሎቹ ናይጄሪያ እና ጋና ጋር ስትደለደል በምድብ አንድ አዘጋጇ ካሜሮን ከሪዮ ኦሎምፒክ ተሳታፊዎቹ ዚምባቡዌ እና ደቡብ አፍሪካ ጋር ተደልድለዋል፡፡

የዘጠኝ ግዜ ውድድሩ አሸናፊ ናይጄሪያ ያለችበት ምድብ ሁለት የሞት ምድብ የተባለ ሲሆን የኤኳቶሪያል ጊኒ ያተገባ ተጫዋች በማሰለፏ ምክንያት ወደ ድድር የተመለሰችው ማሊ በዚው ምድብ ትገኛለች፡፡

ናሚቢያ በ2014 ባዘጋጀችው የአፍሪካ ሴቶች ዋንጫ ናይጄሪያ ሻምፒዮን ሆናለች፡፡ ውድድሩ መክፈቻ ህዳር 10/2008 ካሜሮን ከግብፅ በሚያደርጉት ጨዋታ ይሆናል፡፡

ምድብ አንድ

ካሜሮን (አዘጋጅ)፣ ግብፅ፣ ደቡብ አፍሪካ፣ ዚምባቡዌ

ምድብ ሁለት

ናይጄሪያ፣ ጋና፣ ማሊ፣ ኬንያ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *