ኮንፌድሬሽን ካፕ፡ የግማሽ ፍፃሜ ጨዋታዎች በአቻ ውጤት ተጠናቀዋል

 የአፍሪካ እግርኳስ | 09-01-2009 

የኦሬንጅ ካፍ ኮንፌድሬሽን ካፕ የግማሽ ፍፃሜ ጨዋታዎች ቅዳሜ እና ዕሁድ ሲደረጉ ኤቷል ደ ሳህል ከቲፒ ማዜምቤ 1-1 እንዲሁም ኤምኦ ቤጃያ ከፉስ ራባት ያለ ግብ አቻ ተለያይተዋል፡፡

ቅዳሜ ምሽት ሶስ ላይ በተደረገ ጨዋታ ኤቷል ከማዜምቤ 1 አቻ ተለያይተዋል፡፡ ግብ በማስቆጠር ቅድሚያውን ያየዙት ባለሜዳዎቹ ሲሆኑ በውድድር ዓመቱ መጀመሪያ ውሉን ያደሰው ሃምዛ ላማሃር በ20ኛው ደቂቃ የቱኒዚያ ሻምፒዮኖቹን የመጀመሪያ ግብ ከመረብ አሳርፏል፡፡ ከጨዋታ ጨዋታ መሻሻልን እያሳየ የሚገኘው የሁበርት ቬሉዱ ማዜምቤ በኮትዲቯሩ የመስመር አማካይ ሮጀር አሳሌ የ52ኛ ደቂቃ ግብ ወሳን የሆነ የአቻ ውጤት ይዞ ወደ ሉቡምባሺ ተምልሷል፡፡ በስታደ ቲፒ ማዜምቤ የአምስት ግዜ የአፍሪካ ቻምፒዮኖቹን ማሸነፍ በጣም ከባድ የሆነ ቢሆንም የፋውዚ ቤንዛርቲው ኤቷል ወደ ፍፃሜው ለማለፍ የግድ ማዜምቤን ማሸነፍ አለበት፡፡

picsart_1474277013605

አልጄሪያ ላይ በቤጃያ ከተማ የተገናኙት የሞሮኮው ቻምፒዮን ፉስ ራባት እና ኤምኦ ቤጃያ ለግብ አቻ ተለያይተዋል፡፡ ቤጃያ በምድብ ማጣሪው ሁለት ግቦች ብቻ ተጋጣሚዎቹ ላይ ያሳረፈ ሲሆን በእጅጉ የሳሳው የአጥቂ ክፍሉ ግቦች ማግኘት እየተቸገረ ነው፡፡ ውጤቱ ለሞሮኮ መዲና ክለብ ጥሩ ሲሆን ለፍፃሜ የማለፍ ቅድመ ግምቱንም ማግኘት ችሏል፡፡ የሰሜን አፍሪካ ክለቦች በሜዳው ሲፈትን የነበረው ቤጃያ በራባት ከባድ የሆነ ፈተና ይጠብቀዋል፡፡ ቤጃያ ከቻምፒየንስ ሊጉ የጋናው አሻንቲ ጎልድ እና የቱኒዚያውን ክለብ አፍሪካን ሲያስወጣ በዛማሌክ ተሸንፎ ወደ ምድብ ሳያልፍ ቀርቷል፡፡ ቤጃያ የኮንፌድሬሽን ካፕ ምድብ ውስጥ ሊገባ የቻለው ሃያሉን የቱኒዝ ክለብ ኤስፔራንስን በማሸነፍ ነው፡፡

የመልስ ጨዋታዎች በሳምንቱ መጨረሻ የሚደረጉ ይሆናሉ፡፡

ውጤቶች፡

ኤቷል ስፖርቲቭ ደ ሳህል (ቱኒዚያ) 1-1 ቲፒ ማዜምቤ (ዲ.ሪ. ኮንጎ)

(20’ ሃምዛ ላምሃር | 52’ ሮጀር አሳሌ)

ሞሊዲያ ኦሎምፒክ ቤጃያ (አልጄሪያ) 0-0 ፋት ዩኒየን ስፖርት ራባት (ሞሮኮ)

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *