የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ፕሮግራም ሀሙስ ይፋ ይሆናል

 ፕሪሚየር ሊግ | 09-01-2009 

የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የ2009 የውድድር ዘመን የእጣ ማውጣት ስነ ስርአት በመጪው ሀሙስ መስከረም 12 በካፒታል ሆቴል ይደረጋል፡፡ ፌዴሬሽኑ ከሌሎች አመታት በተሻለ መልኩ ዘንድሮ የውድድሩን ፕሮግራም ከ40 ቀናት ቀደም ብሎ ፕሮግራሙን ይፋ ያደርጋል፡፡

የዕጣ ማውጣት ስነ ስርአቱ ከ03:00 ጀምሮ የፌዴሬሽን ስራ አስፈፃሚ አባላት ፣ የሊግ ኮሚቴ ፣ የክለብ አመራሮችና የቡድን መሪዎች እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው ተሳታፊዎች በተገኙበት ይካሄዳል፡፡

በስነስርዓቱ ላይ ከእጣ ማውጣቱ በተጨማሪ ውይይቶች የሚኖሩ ሲሆን የሚከተሉት አጀንዳዎች ላይ ውይይት ይደረጋል፡፡

* የ2008 የውድድር ዘመን ሪፖርት

* የውድድሩ ደንብ

* ሁሉም ክለቦች የተስፋ ቡድኖችእንዲያቋቁሙ አቅጣጫ ማስያዝ እና የመሳሰሉት ላይ ውይይት ይደረጋል፡፡

ፕሪሚየር ሊጉ ጥቅምት 20 ቀን 2009 የሚጀመር ሲሆን ከ2003 የውድድር ዘመን በኋላ ለመጀመርያ ጊዜ በ16 ክለቦች መካከል ይደረጋል፡፡

Leave a Reply