የሴካፋ ሴቶች ዋንጫ ነገ ይጠናቀቃል

 የሴቶች እግርኳስ | 09-01-2009 

በዩጋንዳ አስተናጋጅነት እየተካሄደ የሚገኘው የሴካፋ ሴቶች ዋንጫ ነገ ኬንያ ከ ታንዛንያ በሚያደርጉት ጨዋታ ይጠናቀቃል፡፡

7 ሃገራት የተሳተፉበትና ከመስከረም 1 ጀምሮ በጂንጃ ከተማ ንጂሩ የቴክኒክ ማዕከል ሲካሄድ የቆየው የሴካፋ ሴቶች ዋንጫ ነገ ሲጠናቀቅ በደረጃ ጨዋታ ኢትዮጵያ ከአስተናጋጇ ዩጋንዳ 07:30 ይጫወታሉ፡፡ ዩጋንዳ በታንዛንያ 4-1 ተሸንፋ ከፍጻሜው የቀረች ሲሆን አስተናጋጅ ከመሆኗ በቀር ለኢትዮጵያ ከባድ ተጋጣሚ ትሆናለች ተብሎ አይታሰብም፡፡ ኢትዮጵያ በበኩሏ በኬንያ 3-2 ተሸንፋ ወደ ፍጻሜው ማለፍ ሳትችል ቀርታለች፡፡

09:30 ላይ ታንዛንያ ከ ኬንያ ለዋንጫ ይገናኛሉ፡፡ ሁለቱ ሃገራት ለዋንጫው ከፍተኛ ግምት ካገኙት መካከል ግንባር ቀደሞቹ የነበሩ ሲሆን እንደተጠበቀውም ለፍጻሜው ተገናኝተዋል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *