የሴቶች እግርኳስ | 10-01-2009
በዩጋንዳ አስተናገዱ እየተካሃደ ባለው የሴካፋ ሴቶች ዋንጫ የኢትዮጵያ ሴቶች ብሄራዊ ቡድን ዩጋንዳን 4-1 በመርታት በ3ኝነት ውድድሩን አጠናቋል፡፡
07:30 ላይ በጀመረው የደረጃ ጨዋታ ግብ በማስቆጠር ቅድሚያውን የያዙት አስተናጋጆቹ ሲሆኑ በ5ኛው ደቂቃ ሀሲፋ ናሱማ የግቡ ባለቤት ናት፡፡ ይህ ግብ ለሀሲፋ በውድድሩ ያስቆጠረችው 5ኛ ግብ ሆኖ ተመዝግቧል፡፡
ኢትዮጵያ አቻ ለመሆን ብዙ ደቂቃ ያልፈጀባት ሲሆን በ16ኛው ደቂቃ ረሂማ ዘርጋ ሉሲዎቹን አቻ አድርጋለች፡፡ ቡድኖቹ ለእረፍት ከመውጣታቸው 1 በፊት ረሂማ ኢትዮጵያን መሪ ስታደርግ በ73ኛው ደቂቃ ደግሞ ሐት-ትሪክ የሰራችበትን ግኳስ ከመረብ አሳርፋለች፡፡ ሎዛ አበራ በ78ኛው ደቂቃ የሉሲዎቹን ቀሪ ግብ ስታስቆጥር የግብ ድምሯን 5 በማድረስ ከከፍተኛ ግብ አስቆጣሪዎች ተርታ ተሰልፋለች፡፡
ውድድሩ በአሁኑ ሰአት በኬንያ እና ታንዛንያ መካከል የፍጻሜ ጨዋታ እያስተናገደ ይገኛል፡፡