ፕሪሚየር ሊግ| 12-01-2009 

የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የ2009 የውድድር ዘመን መርሃ ግብር ዛሬ በካፒታል ሆቴል እና ስፓ በተደረገ ስነስርአት ይፋ ሆኗል፡፡

በአጣ ማውጣት ስነስርአቱ ላይ የፌዴሬሽኑ አመራሮች ፣ የክለብ ተወካዮች እና የቀድሞ ታላላቅ ተጫዋቾች የተገኙ ሲሆን በወጣው እጣ መሰረት የመጀመርያ ሳምንት ተጋጣሚዎች የሚከተሉት ሆነዋል፡-

ቅዱስ ጊዮርጊስ ከ አርባምንጭ ከተማ (አአ)

ሲዳማ ቡና ከ ፋሲል ከተማ (ይርጋለም)

ኢትዮጵያ ቡና ከ ደደቢት (አአ)

ወላይታ ድቻ ከ መከላከያ (ቦዲቲ)

ሀዋሳ ከተማ ከ አዲስ አበባ ከተማ (ሀዋሳ)

ጅማ አባ ቡና ከ ኢትዮ ኤሌክትሪክ (ጅማ)

ወልድያ ከ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ (ወልድያ)

አዳማ ከተማ ከ ድሬዳዋ ከተማ (አዳማ)

picsart_1474560982422

በስነስርአቱ ስላሳለፍነው የውድድር ዘመን ሙሉ ሪፖርት በሚመለከታቸው አካላት የቀረበ ሲሆን በቀጣይ የውድድር ዘመናት በሚኖሩ አዳዲስ ለውጦች ላይም ፌደሬሽኑ ከክለብ አመራሮች ጋር ውይይት ተደርጓል፡፡ በ2009 ዓ.ም የውድድር ዘመን ላይም የደንብ ማሻሻያዎች ተደርገዋል፡፡

ከተደረጉት ማሻሻያዎች መካከል በሊጉ ከ25 ነጥብ በታች የሚያስመዘግብ ክለብ ወደ ብሄራዊ ሊግ እንዲወርድ በሚያደርገው አዲስ ደንብ ላይ ስምምነት ያልተደረሰ በመሆኑ ወደፊት ውሳኔ እንደሚሰጥበት ተነግሯል፡፡ በ2009 ዓ.ም ላይ በከፍተኛ ሊጉ ተሳታፊ ከሚሆኑ ክለቦች ወደ ዋናው የ2010 የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የሚያድጉ ክለቦች ቁጥር ወደ ሶስት ሲቀነስ በሁለት ምድብ በሚከናውነው የከፍተኛ ሊግ ውድድር ላይ ከሁለቱም ምድቦች አንደኛ የወጡ ሁለቱ ክለቦች በቀጥታ ያድጋሉ፡፡ ሁለተኛ የሚወጡት ሁለቱ ክለቦች በሚያደርጉት የመለያ ጨዋታ ሶስተኛ ክለብ ሆነው ወደ ፕሪሚየር ሊግ ያድጋሉ፡፡

ውድድሩን የሚዳኙ ዳኞችን በተመለከተ ዋናው ዳኛ ጨዋታውን የማይመራ ከሆነ በአዲሱ የተሻሻለው ህግ መሰረት የመጀመሪያ ረዳት ዳኛው ጨዋታውን የሚመራ ሲሆን የመጀመሪያ ረዳት ዳኛው ጨዋታውን መምራት የማይችልበት አጋጣሚ ቢኖር ሁለተኛ ረዳት ዳኛው ጨዋታውን እንደሚመራ በውይይቱ ላይ ተገልጿል፡፡ ጨምረውም በ2009 ዓ.ም የዳኞችን ብቃት ለማሳደግ የተለያዩ ትምህርቶች ለዳኞች እየተሰጠ እንደሆነ ተናድረዋል፡፡

picsart_1474560940061

በውይይቱ ላይ ብዙዎቹን የክለብ አመራሮች ሲያጋግር የነበረው ከ20 ዓመት በታች ከሚጫወቱ ተጨዋቶች መካከል ወደ ዋናው ቡድን የሚገቡተጨዋቾችን ቁጥር የመወሰን ጉዳይ ዋነኛው ነበር፡፡ በፌደሬሽኑ በኩል ከ20 ዓመት በታች ወደ ዋናው ክለብ የሚያድጉ ተጨዋቾችን በቁጥር የገደበ ሲሆን ክለቦች ደግሞ በቁጥር መገደብ እንደሌለበት ሲነገሩ ተስተሏል፡፡ ፌደሬሽኑም በመጨረሻ አምስት ብሎ በቁጥር የገደበውን የተጫዋቾች ቁጥር ወደፊት እንደሚያጤነው እና በቅርቡ ውሳኔ እንደሚሰጥበት አስታውቋል፡፡

የሊጉ ቻምፒዮን ለሚሆነው ቡድን የሽልማት አሰጣጥ ጉዳይ ላይ የሚሰጠው የዋንጫ አይነት ፣ መጠን እና ቅርፅ ተመሳሳይ እንደሚሆን ተነግሯል፡፡ በተመሳሳይ ለውድድሩ ኮከብ ተጨዋቾች ኮከብ ግብ አግቢ ፣ ኮከብ ዳኞች እና ኮከብ ግብ ጠባቂዎች የሚሰጠው የገንዘብ ሽልማት ከወዲሁ እንደሚገለፅ እና የውድድሩ አሸናፊ የሚሆነው ቡድንን ጨምሮ ሁለተኛ እና ሶስተኛ ለሚወጣው ክለብ የሚሰጠው የገንዘብ ሽልማት ከወዲሁ እንደሚገለፅ ተነግሯል፡፡

በ2009 በሊጉ ላይ የሚሳተፉ ክለቦች የመመዝገቢያ የገንዘብ መጠን ከ10ሺ ወደ 25ሺ ብር እንዳደገ ዛሬ ቢገለፅም ነገር ግን ክለቦች ይህንን ጉዳይ አብዛኞቹ ክለቦች እንዳልተቀበሉት በውይይቱ ላይ ለመታሰብ ተችሎዋል፡፡ ፌደሬሽኑም ይህንን ጉዳይ እንደሚያስብበት እና በቀጣይ የሚመለከታቸው አካላት ስለ ጉዳዩ ውሳኔ እንደሚያደርስ ተናግሯል፡፡

  የፕሪሚየር ሊጉ 1ኛ ዙር መርሃ ግብር ነገ እናቀርባለን 

Leave a Reply