የኢትዮጵያ ሀ-17 ብሄራዊ ቡድን ለማሊው የመልስ ጨዋታ ዝግጅቱን ቀጥሏል

  የወጣቶች እግርኳስ | 14-01-2009 

የኢትዮዽያ ከ17 አመት በታች ብሄራዊ ቡድን ከማሊ ጋር ለሚያደርገው የአፍሪካ ከ17 አመት በታች ዋንጫ የመጨረሻ ማጣሪያ ወሳኝ የመልስ ጨዋታ ዝግጅቱን አጠናክሮ ቀጥሏል፡፡

ከባማኮ መልስ ማረፊያቸውን አንፋራሲስ ሆቴል ያደረጉት ቀይ ቀበሮዎቹ ለመልሱ ጨዋታ ዝግጅት ከጀመሩ አራተኛ ቀናቸውን አስቆጠረዋል፡፡ ዛሬ ረፋድ ላይም በአበበ በቂላ ስታድየም 20 ተጨዋቾችን በመያዝ ልምምዱን አከናዉኗል፡፡

በፈጣን እንቅስቃሴ ውስጥ የመጨረሻ ሳጥን ውስጥ በመግባት ጎል የማስቆጠር ልምምዶች የዛሬው መርሃ ግብር አካል ነበሩ፡፡

picsart_1474721801847

ከታዳጊ ብሄራዊ ቡድኑ ጋር በተያያዘ በማሊው የመጀመርያ  ጨዋታ ላይ ጉዳት ያጋጠመው ተከላካዩ ሳሙኤል ዛሬ ቀለል ያለ ልምምድ ያደረገ ሲሆን የቡድኑ  ቁልፍ ተጨዋች የሆነው የሐረር ሲቲው ሚኪያስ መኮንን በሁለት ቢጫ ምክንያት ከቡድኑ ውጪ መሆኑ በቡድኑ ላይ አሉታዊ ተፅእኖ እንዳያሳድር ተሰግቷል፡፡

በኢትዮዽያ እና በማሊ መካከል የሚደረገው የመልስ ጨዋታ እሁድ መስከረም 22 ቀን 2009 በ10:00 አዲስ አበባ ስታድየም ላይ የሚካሄድ ይሆናል፡፡ አዲስ አበባ ስታድየምን ለጨዋታው ዝግጁ ለማድረግ በዕረፍት ቀናት ጭምር በመሰራት ላይ እንደሆነ ለመመልከት ችለናል፡፡

picsart_1474721866537

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *