ደቡብ ካስቴል ዋንጫ | 16-01-2009 

የደቡብ ክልል እግርኳስ ፌዴሬሽን የሚያዘጋጀው የደቡብ ካስቴል ዋንጫ ላይ የሚካፈሉ 7 ቡድኖች ተለይተው ታውቀዋል፡፡

ሶከር ኢትዮጵያ ከፌዴሬሽኑ ባረጋገጠችው መረጃ መሰረት ከሀዋሳ ከተማ ፣ ወላይታ ድቻ ፣ ሲዳማ ቡና እና አርባምንጭ ከተማ በተጨማሪ የሚካፈሉት ክለቦች ኢትዮጵያ ቡና ፣ ድሬዳዋ ከተማ እና ፋሲል ከተማ ሆነዋል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ ዋንጫ ላይ እንደማይካፈል ያስታወቀው ኢትዮጵያ ቡና የቅድመ ውድድር ዘመን ዝግጅቱን በሀዋሳ እየያደረገ እንደመገኘቱ በደቡብ ካስቴል ዋንጫ ላይ ሊካፈል እንደሚችል ተገምቶ የነበረ ሲሆን እንደፌዴሬሽኑ መረጃ ከሆነ ኢትዮጵያ ቡና የመሳተፍ ግብዣውን ተቀብሏል፡፡ ሶከር ኢትዮጵያ ስለ ጉዳዩ ለክለቡ ባቀረበችው ጥያቄ ግን ክለቡ የደረሰበትን ውሳኔ በራሱ የፌስቡክ ገጽ እንደሚያሳውቅ በመግለጽ መረጃ ከመስጠት ተቆጥቧል፡፡

የከፍተኛ ሊጉ ቻምፒዮን ፋሲል ከተማ በውድድሩ ላይ ለመሳተፍ ጥያቄ አቅርቦ የነበረ ሲሆን በአወዳዳሪው አካል ተቀባይነት አግኝቷል፡፡ በአምናው ውድድር ላይ የተሳተፈው ድሬዳዋ ከተማ ደግሞ ቀደም ብሎ መሳተፉ የተረጋገጠ ክለብ ነው፡፡

የደቡብ ካስቴል ዋንጫ መስከረም 24 የሚጀምር ሲሆን መስከረም 23 በሀዋሳ ሴንትራል ሆቴል ከቀኑ 08:00 ጀምሮ የእጣ ማውጣት ስነ ስርአት ይካሄዳል፡፡

1 Comment

  1. ከአዲስ አበባ ዋንጫ የደቡብ ምርጥ ይሆናል
    የሙልዬ መታሠቢያ ዋንጫ እንዳለ ሆኖ!!!

Leave a Reply