ብሄራዊ ሊግ | 18-01-2009
የ2009 የውድድር ዘመን የኢትዮዽያ ብሄራዊ ሊግ ህዳር 11 ቀን 2009 እንደሚጀምር የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን ብሄራዊ ሊግ ኮሚቴ ለክለቦች በላከው ደብዳቤ አስታውቋል፡፡
ውድድሩ ከመጀመሩ 1 ወር በፊት ጥቅምት 6 ላይ ሁሉም ተሳታፊ ቡድኖች በተገኙበት የ2008 የውድድር ዘመን ሪፖርት እና ግምገማ እንዲሁም የ2009 የውድድር ደንብ ለውይይት ይቀርባል፡፡
በጉባዔው ላይ በዋነኝነት ለውይይት ይቀርባል ተብሎ የሚጠበቀው አጀንዳ አንዱ አምና በሰባት ዞን ተከፍሎ ከነበረው ውድድር ዘንድሮ ወደ አራት ወይም አምስት ዞኖች በመቀነስ ወጣ ገባ የነበረውን የዞን ተሳታፊዎች ቁጥር በሁሉም ዞኖች ላይ ተቀራራቢ ለማድረግ የታሰበው ሀሳብ ነው፡፡
በዘንድሮው የውድድሩ ተሳታፊዎች ቁጥር ከአምናው ከፍ በማድረግ በ59 ክለቦች መካከል ለማካሄድ እንደታሰበ ለማወቅ ተችሏል፡፡