የአዲስ አበባ ከተማ ዋንጫ እጣ ማውጣት ስነ ስርአት ነገ ይደረጋል

የአዲስ አበባ እግርኳስ ፌዴሬሽን ለ11ጊዜ የሚያካሂደው የአዲስ አበባ ከተማ ዋንጫ የእጣ ማውጣት ስነ-ስርዓት ነገ በኢትዮጵያ ሆቴል ከቀኑ 5:00 ጀምሮ እንደሚከናወን የአዲስ አበባ እግር ኳስ ፌደሬሽን አሰታውቋል።

ስድስት የአዲስ አበባ ክለቦች እና ሁለት ተጋባዥ ክለቦችን በመጨመር ከመስከረም 28 እስከ ጥቅምት 13 በሚከናወነው ይህ ውድድር ከአዳማ ከተማ በተጨማሪ የሚጋበዘውን ክለብ ማወቅ እንዳልተቻለ የተገለጸ ሲሆን ምናልባት እስከ ዛሬ አመሻሽ የማይታወቅ ከሆነ ሰባቱ ክለቦች ብቻ ውድድሩ ላይ እንደሚሳተፉ ከፌደሬሽኑ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

ፌዴሬሽኑ በትላንትናው እለት ከክለብ አመራሮች ጋር የውድድሩን ደንብ በተመለከተ ውይይት የተደረገ ሲሆን ካለፉት ውድድሮች የተለየ አዲስ ደንብ በዘንድሮው ውድድር ላይ እንዳልተካተተ ለማወቅ ተችሏል።

ፌደሬሽኑ ውድድሩን በቀጥታ የቴሌቪዥን ስርጭት ለማስተላለፍ ከኢቢሲ ጋር ድርድር እያደረገ መሆኑ የታወቀ ሲሆን እስከ አራት ጨዋታዎች ለማስተላለፍ እንደታሰበም ታውቋል።

picsart_1475236700426

Leave a Reply