ኢትዮጵያ U-17 ከ ማሊ U-17 : ቀጥታ የጽሁፍ ስርጭት

ተጠናቀቀኢትዮጵያ1-2ማሊ

72′ ፋሲል አለማየሁ | 3′ ሲቢሪ ኬይታ , 90+1′ ሞሃማኒ ቱሬ

ድምር ውጤት 1-4


ተጠናቀቀ !!!
ጨዋታው በማሊ 2-1 አሸናፊነት ተጠናቋል፡፡ የ2015 ቻምፒዮኗ ማሊ በ4-1 ድምር ውጤት አሸንፋ ማዳጋስካር ለምታስተናግደው የ2017 የአፍሪካ ከ17 አመት በታች ዋንጫ አልፋለች፡፡

ጎልልል
90+1′ ሞሃማኒ ቱሬ በመልሶ ማጥቃት ማሊን መሪ አድርጓል፡፡

ተጨማሪ ደቂቃ
መደበኛው የጨዋታ ክፍለ ጊዘዜ ተጠናቆ 4 ደቂቃ ተጨምሯል፡፡

የተጫዋች ለውጥ – ማሊ
86′
ጄሞሳ ትራኦሬ ወጥቶ ማማዱ ሳሊያ ሳኮ ገብቷል፡፡

ቢጫ ካርድ
84′
ማማዱ ሳማኬ በፋሲል ላይ በሰራው ጥፋት የማስጠንቀቅያ ካርድ ተመልክቷል፡፡

80′ ማሊዎች ኳሱን በመቆጣጠር ጨዋታውን አረጋግተውታል፡፡ የኢትዮጵያ አብዛኛዎቹ ተጫዋቾች በራሳቸው የሜዳ ክፍል ይገኛሉ፡፡

ጎልልል !! ኢትዮጵያ
72′ ፋሲል አለማየሁ ከመስመር የተሻገረውን ኳስ ተጠቅሞ ኢትዮጵያን አቻ ያደረገች ግብ ከመረብ አሳርፏል፡፡

የተጫዋች ለውጥ – ኢትዮጵያ
70′
አክሊሉ አለሙ ወጥቶ ምንተስኖት ዮሴፍ ገብቷል፡፡

63′ ሰይቡ ሴኖ ከርቀት አክርሮ የመታውን ኳስ ኦኛ ጨርፎ አውጥቶቷል፡፡

60′ ኢትዮጵያ በ2ኛው አጋማሽ የተሻለ እንቅስቃሴ እያደረገች ትገኛለች፡፡ በተደጋጋሚ ኸደ ማሊ የግብ ክልል በመጠጋት ላይም ትገኛለች፡፡

የተጫዋች ለውጥ – ኢትዮጵያ
57′
ቃልኪዳን ዘላለም ወጥቶ ዳግማዊ አርአያ ገብቷል

55′ ከማዕዘን የተሻማኽን ኳስ ጃፋር በግንባሩ ገጭቶ ግብ ጠባቂው የሱፍ አውጥቶታል፡፡

54′ አክሊሉ አለሙ ያሻማውን ኳስ ቃልኪዳን ሳይደርስበት ቀርቷል፡፡ ጥሩ አጋጣሚ ነበር፡፡

የተጫዋች ለውጥ – ማሊ
51′
ሴሜ ካማራ ወጥቶ ማሃማኔ ቱሬ ገብቷል፡፡

የተጫዋች ለውጥ – ማሊ
46′
ሀጂ ድራሜ ወጥቶ ሰይቡ ሰኖው ገብቷል፡፡

ተጀመረ!!
ሁለተኛው አጋማሽ የጨዋታ ክፍለ ጊዜ በማሊ አማካኝነት ተጀምሯል፡፡ በመጀመርያው አጋማሽ ተዳክማ የቀረበችው ኢትዮጵያ በድምር ውጤት ለማለፍ በ2ኛው አጋማሽ 4 ግቦች አስቆጥራ ግብ አለማስተናገድ ይጠበቅባታል፡፡


እረፍት!
የመጀመርያው አጋማሽ በማሊ መሪነት ተጠናቋል፡፡

የተጫዋች ለውጥ – ኢትዮጵያ
45+2′
ረመዳን የሱፍ ወጥቶ ፋሲል አበባየሁ ገብቷል፡፡

44′ ቃልኪዳን ከርቀት የመታው ኳስ አግዳሚውን ሲመልስ በአቅራቢያው የነበሩት የኢትዮጵያ ተጫዋቾች ያገኙትን መልካም አጋጣሚ መጠቀም አልቻሉም፡፡

41′ ሴማ ካማራ በመልሶ ማጥቃት የመጣውን ኳስ ሞክሮ ኦሜ አድኖበታል፡፡

38′ የማሊ ተጫዋቾች በተደጋጋሚ በመውደቅ ላይ ይገኛሉ፡፡

34′ ሲቢሪ ኬይታ ለኢትዮጵያ ተከላካዮች ፈታኝ እንቅስቃሴ እያደረገ ይገኛል፡፡

27′ ሲቢሪ ኬይታ 3 ተጫዋቾች አታሎ የሞከረውን ኳስ ኦኛ አድኖታል፡፡

20′ ቃልኪዳን ዘላለም የመታኽ ቅጣት ምት በግቡ አናት ወደ ውጪ ወጥቷል፡፡

18′ ኢትዮጵያ ወደ ማሊ የግብ ክልል ሰብራ መጠጋት አልቻለችም፡፡

12′ ሲቢሪ ኬይታ ከሳጥን ውስጥ የመታው ኳስ ወደ ውጪ ወጥቷል፡፡

ቢጫ ካርድ
11′
ጫላ ተሺታ የማስጠንቀቂያ ካርድ ተመልክቷል፡፡

ጎልልል!!!!
3′ ሲቢሪ ኬይታ ማሊን ቀዳሚ ያደረገችውን ግብ አስቆጥሯል፡፡

1′ አቡበከር ነስሩ የመታውን ቅጣት ምት ግብ ጠባቂው ኮይታ በቀላሉ ይዞታል፡፡

ተጀመረ!!!
ጨዋታው በኢትዮጵያ አማካኝነት ተጀምሯል፡፡


09:58 የኢትዮጵያ ብሄራዊ መዝሙር እየተዘመረ ይገኛል፡፡

09:57 የማሊ ብሄራዊ መዝሙር እየተዘመረ ይገኛል፡፡

09:55 ሁለቱም ቡድኖች ወደ ሜዳ ገብተዋል፡፡

08:53 ጨዋታው ሊጀመር ጥቂት ደቂቃዎች ቢቀሩትም አዲስ አበባ ስታድየም የተገኘው ተመልካች በጣም ጥቂት ነው፡፡


የኢትዮጵያ አሰላለፍ

1 ኦኛ ኦመኛ (ግብ ጠባቂ)
2 እዮብ አለማየሁ
3 ሳሙኤል ተስፋዬ (አምበል)
4 ጌታሰጠኝ ሸዋ
6 ጃፋር ሙደሲር
11 አቡበከር ነስሩ
13 አክሊሉ አለሙ
14 ጫላ ተሺታ
16 እሱባለው ጌታቸው
17 ቃልኪዳን ዘላለም
18 ረመዳን የሱፍ

ተጠባባቂዎች

12 ፋሲል ገብረሚካኤል (ግብ ጠባቂ)
5 አማኑኤል አዲሱ
6 ሎክ ፓውሊንሆ
7 ፍቃደስላሴ ደሳለኝ
8 ማትያስ ወልደአረጋይ
9 ፋሲል አበባየሁ
10 ዳግማዊ አርአያ
15 ምንተሰኖት ዮሴፍ


የማሊ አሰላለፍ

16 የሱፍ ኮይታ (ግብ ጠባቂ)
3 ድጄሙሳ ትራኦሬ
4 ፎዴ ኮናቴ
5 ማማዲ ቶፋና
6 መሃመድ ካማራ (አምበል)
7 ሀጂ ድራሚ
9 ሴሚ ካማራ
10 ሪብሪ ኬይታ
15 ቦባካር ዶምቢያ
17 ማማዱ ሳማኬ
18 ኢብራሂም ካኔ

ተጠባባቂዎች
1 አልካሊፋ ኩሊባሊ (ግብ ጠባቂ)
2 ማማዱ ሳሊ ሳኮ
8 አብዱላሂ ጃቦ
11 ማሃማኔ ቱሬ
12 ሲያቡ ሴኔ
13 ባካሪ ትራኦሬ
14 ማማዱ ትራኦሬ


09:15 የማሊ ብሄራዊ ቡድን ተጫዋቾች ወደ ሜዳ በመግባት ሰውነታቸውን እያፍታቱ ይገኛሉ፡፡

09:20 የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ተጫዋቾች ወደ ሜዳ በመግባት ሰውነታቸውን እያፍታቱ ይገኛሉ፡፡

1 Comment

Leave a Reply