ሙሉጌታ ምህረት በታላቅ ክብር ተሸኘ

ባለፉት 16 አመታት በኢትዮጵያ እግር ኳስ ላይ አሻራቸውን ካሳረፉት ተጨዋቾች አንዱ የሆነው ሙሉጌታ ምህረት ዛሬ በሀዋሳ ኢንተርናሽናል ስታድየም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ፣ የሙሉጌታ ምህረት ቤተሰቦች ፣  አድናቂዎች እና የስፖርት ቤተሰቦች በተገኙበት በታላቅ ድምቀት በክብር ተሸኝቷል፡፡

ለመሸኛው ሁለት ጨዋታዎች የተዘጋጁ ሲሆን 08:00 ላይ በተካሄደው የመጀመርያ ጨዋታ ኢትዮዽያ ቡና ጋቶች ፓኖም ባስቆጠራት ግሩም ግብ ሲዳማ ቡናን 1-0 በማሸነፍ የተዘጋጀው የክብር ዋንጫ አሸናፊ ሆኗል፡፡

በጨዋታው እረፍት ሰአት ላይ የኢትዮዽያ ቡና ደጋፊዎች ማህበር ለሙሉጌታ ምህረት ያላቸውን አክብሮት ለመግለፅ ያቀረቡለትን ቶርታ ኬክ  በጋራ በመሆን ቆርሰዋል፡፡

picsart_1475425770162

10:00 በቀጠለው ሁለተኛ ጨዋታ ቅዱስ ጊዮርጊስ ከሀዋሳ ከተማ ተጫውተዋል፡፡ ሙሉጌታ ባስጀመረው ጨዋታ ሁለቱም ቡድኖች መደበኛውን የጨዋታ ክፍለ ጊዜ 1-1 ያጠናቀቁ ሲሆን አዳነ ግርማ (ፍ/ቅ/ም) ለፈረሰኞቹ ፤ መድሀኔ ታደሰ ለሀዋሳ ጎሎቹን አስቆጥረዋል፡፡

አሸናፊውን ለመለየት በተሰጠው የመለያ ምት ቅዱስ ጊዮርጊስ 5-4 በማሸነፍ ሌላውን የክብር ዋንጫ አሸናፊ ሆኗል፡፡

picsart_1475425719760

ከጨዋታዎቹ ፍጻሜ በኋላ የሽልማት ፕሮግራም የተካሄደ ሲሆኖ የቅዱስ ጊዮርጊስ ስፖርት ማህበር ፕሬዝዳንት አቶ አብነት ገብረመስቀል በተወካያቸው አማካኝነት ለሙሉጌታ ምህረት የ75,000 የገንዘብ ስጦታ አበርክተውለታል፡፡ በተጨማሪም የኢትዮዽያ እና የደቡብ ክልል የዳኞች ማህበር ለሙልጌታ ምህረት የዋንጫ ሽልማት የሰጡ ሲሆን በዕለቱም የተለያዮ ማህበራት ስጦታዎችን አበርክተውለታል፡፡

በመጨረሻም በ16 አመት የእግር ኳስ ህይወቱ ከጎኑ በመሆን ለደገፉት እና ላበረታቱት እንዲሁም ለዝግጅቱ መሰካት እና ማማር ለተባበሩት ሁሉ ምስጋና በማቅረብ የሽኝት መርሃ ግብሩ ፍፃሜ ሆኗል፡፡

picsart_1475425613387

Leave a Reply