የደቡብ ካስትል ዋንጫ የምድብ ድልድል ይፋ ሆነ

  ደቡብ ካስትል ዋንጫ | 23-01-2009 

በሰባት ክለቦች መካከል ከመስከረም 24 እስከ ጥቅምት 3 ቀን 2009 በሀዋሳ ከተማ የሚካሄደው የደቡብ ክልል ካስትል ዋንጫ የምድብ ድልድል ይፋ ሆኗል፡፡

የደቡብ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ምክትል ስራ አስኪያጅ አቶ ደምመላሽ ይትባረክ ፣ ዳኞች ፣ ታዛቢዎች እና የክለብ ተወካዮች በተገኙበት በሴንትራል ሀዋሳ ሆቴል የዕጣ ማውጣት ስነ ስርአት የተካሄደ ሲሆን በተካሄደው ውይይትም ውድድሩ በኢትዮዽያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ህግ መሰረት እንደሚመራ እና አዲሱ የፊፋ ህግ ተግባራዊ እንደሚሆን ተገልጿል፡፡

በውድድሩ ላይ ተጋባዥ ቡድን አሸናፊ ቢሆን ሌላ የተዘጋጀ ዋንጫ እንደሚያነሳ የተገለጸ ሲሆን የኮኮቦች ምርጫም እንደሚኖር ታውቋል፡፡

የምድብ ድልድል

ምድብ ሀ

ፋሲል ከተማ

ኢትዮዽያ ቡና

ሲዳማ ቡና

ወላይታ ድቻ

ምድብ ለ

አርባምንጭ ከተማ

ድሬዳዋ ከተማ

ሀዋሳ ከተማ

የመክፈቻ ጨዋታው ነገ መስከረም 24 በሀዋሳ ሰው ሰራሽ ሜዳ 09:00 ሀዋሳ ከተማ ከ አርባምንጭ የሚጫወቱ ይሆናል፡፡

በተጨማሪም ሁሉም ውድድሮች በሀዋሳ ሰው ሰራሽ ሜዳ ላይ እንደሚካሄዱ ለማወቅ ተችሏል፡፡


ውድድሩን የተመለከቱ ዘገባዎች ከስፍራው እንድናቀርብ የተባበረን እና በሆቴል በመልካም መስተንግዶ ድጋፍ ላደረገልን ባለ አራት ኮከቡ ሴንትራል ሀዋሳ ሆቴል ምስጋና እናቀርባለን፡፡

Leave a Reply