ደቡብ ካስቴል ዋንጫ ዛሬ ሲጀመር አርባምንጭ ድል ቀንቶታል

  ደቡብ ካስትል ዋንጫ | 24-01-2009 

የደቡብ ክልል ካስትል ዋንጫ ዛሬ በይፋ ሲጀመር በመክፈቻው አርባምንጭ ከተማ ድል ቀንቶታል፡፡

በርካታ ቁጥር ያለው ተመልካች በታደመመበት የዛሬው የመክፈቻ ጨዋታ በቢሾፍቱ ከተማ በኢሬቻ በአል ላይ ህይወታቸው ላለፉት ወገኖች የህሊና ፀሎት በማድረግ የታሰበ ሲሆን አርባምንጭ ባለሜዳው ሀዋሳን አሸንፎ ውድድሩን በድል ከፍቷል፡፡

ጠንካራ ፉክክር በታየበት ጨዋታ የአርባምንጭን ብቸኛ የአሸናፊነት ጎል በመጀመርያው አጋማሽ 40ኛ ደቂቃ ላይ በግሩም ሁኔታ ገ/ሚካኤል ያዕቆብ አስቆጥሯል፡፡

ውድድሩ ነገ ሲቀጥል በምድብ ሀ 08:00 ላይ ፋሲል ከተማ ከ ወላይታ ድቻ ፤ 10:00 ላይ ኢትዮዽያ ቡና ከ ሲዳማ ቡና የሚጫወቱ ይሆናል፡፡ ኢትዮጵያ ቡና ከሲዳማ ቡና ባለፈው እሁድ ለሙሉጌታ ምህረት መሸኛ የወዳጅነት ጨዋታ አድርገው ቡና በጋቶች ፓኖም ግብ 1-0 ማሸነፉ የሚታወስ ነው፡፡


picsart_1475599616679

ውድድሩን በሀዋሳ ተገኝተን እንድንዘግብ በመልካም መስተንግዶ ድጋፍ ላደረገልን ባለ አራት ኮከቡ ሴንትራል ሀዋሳ ሆቴል ከፍተኛ ምስጋና እናቀርባለን፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *