የኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪምየር ሊግ ጨዋታዎች ይፋ ሆነዋል

ጥቅምት 27 ለሚጀመረው የኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪምየር ሊግ የዕጣ ማውጣት ስነ ስርዓት ማክሰኞ በካፒታል ሆቴል እና ስፖ ተደርጓል፡፡ ከዕጣ ማውጣቱ አስቀድሞ ተሳታፊ ክለቦች እና ፌድሬሽኑ በውድድሩ ደንብ ላይ የተወያዩ ሲሆን የ2008 የውድድር ዓመት አፈፃፀም ሪፖርት ቀርቧል፡፡
በሪፖርቱ ውድድሩ ተተኪ ሴት ተጫዋቾች መገኘታቸውን እና ክለቦች ለሴቶች ውድድር ትኩረት በመስጠት መሳተፋቸው እንደጠንካራ ጎን የተነሳ ሲሆን አነስተኛ የተመልካች ቁጥር፣ የስታዲየም ገቢ ተጠቃሚነት አለመኖር እና የዳኝነት ችግሮች ደካማ ጎኖቹ ነበሩ ተብሏል፡፡

ፕሪምየር ሊግ ከዘንድሮው ውድድር አንስቶ በሁለት ምድብ በመከፈል የሚደረግ ይሆንል፡፡ የሰሜን ማዕከላዊ እና ደቡብ ምስራቅ ዞን ተብሎ ሲደረግ የነበረበት ሁኔታ ቀርቶ ክለቦች በሁለት ምድብ ተክፍለው ውድድራቸውን የሚያከናውኑ ይሆናል፡፡ በዕጣ ማውጣት ስነ ስርዓቱን በክብር እንግድነት የተገኙት የቀድሞ የሉሲዎቹ አሰልጣኝ በለጥሽ ገብረማሪያ ነበሩ፡፡

የዓምና ሻምፒዮኑ ደደቢት እና ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የምድብ አባቶች ሁነዋል፡፡ በፈረሱ ክለቦች ምትክ ሌሎች 5 ክለቦች ወደ ውድድር መምጣት ችለዋል፡፡ ሙገር ሲሚንቶ የፈረሰ ሲሆን ዳሽን ቢራ ጥረት ኮርፖሬት ባህርዳር በሚል ተሰይሟል፡፡

በአዲስ አበባ የሴቶች ከፍተኛ ዲቪዚዮን ሲወዳደሩ የነበሩት አቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ የኢትዮጵያ ወጣቶች ስፖርት አካዳሚ እና ቦሌ ክፍለ ከተማ እንዲሁም አዲስ የተመሰረተው አዲስ አበባ ከተማ ከደቡቡ ክለብ ጌዲዮ ዲላ ጋር ፕሪምየር ሊጉን የተቀላቀሉ አዲስ ክለቦች ናቸው፡፡

በሁለት ምድብ ለመክፈል ያስፈለገው ከክለቦቹ የፋይናንስ አቅም እና የማጠቃለያ ውድድር ከማስቀረት አንፃር እንተደረገ ለማወቅ ተችሏል፡፡

በ2009 የውድድር ዘመን የማጠቃለያ ውድድር እንደማይኖር ታውቋል፡፡ የምድብ አሸናፊዎች ለሻምፒዮንነት የሚጫወቱ ሲሆን በሁለተኝነት የሚጨርሱት ደግሞ ለደረጃ እንደሚጫወቱ የወጣው አዲሱ ደንብ ያስረዳል፡፡ በ2010 የውድድር ዘመን ፕሪምየር ሊጉ በሁለት ተክፍሎ አንደኛ እና ሁለተኛ ዲቪዚዮን በመባል የሚካሄድ ይሄናል፡፡ በዚህም ሂደት መውረድ እና መውጣት የሚኖር ይሆናል፡፡ በ2009 የውድድር ዘመን የተሻለ ውጤት የሚመጡ 10 ክለቦች ወደ አንደኛ ዲቪዚዮን ሲገቡ የተቀሩት አስሩ ደግሞ ወደ ሁለተኛ ዲቪዚዮን የሚወርዱ ይሆናል፡፡

የምድብ 1 አንደኛ ሳምንት ጨዋታዎች
ኢትዮጵያ ቡና ከ ደደቢት
ጥረት ኮርፖሬት ባህርዳር ከ ኢትዮጵያ ወጣቶች ስፖርት አካዳሚ
አዳማ ከተማ ከ እቴጌ
መከላከያ ከ ቦሌ ክፍለ ከተማ
ድሬዳዋ ከተማ ከ ኢትዮ ኤሌክትሪክ

የምድብ 2 አንደኛ ሳምንት ጨዋታዎች
ቅድስት ማሪያም ዩኒቨርሲቲ ከ ልደታ ክፍለ ከተማ
ቅዱስ ጊዮርጊስ ከ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ
አርባምንጭ ከተማ ከ አዲስ አበባ ከተማ
ጌዲዮ ዲላ ከ አቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ
ሲዳማ ቡና ከ ሃዋሳ ከተማ

Leave a Reply