ኢትዮጵያ ቡና ከ ድሬዳዋ ከተማ – ቀጥታ የፅሁፍ ስርጭት

FTኢትዮጵያ ቡና1-2ድሬዳዋ ከተማ

56′ ሳሚ ሳኑሚ | 6’ፍቃዱ ወርቁ 37′ ቴድሮስ ሁሴን

         ቀጥታ የጽሁፍ ስርጭት        


ተጠናቀቀ
ጨዋታው በድሬዳዋ ከተማ አሸናፊነት ተጠናቋል፡፡ የአሰልጣኝ ዘላለም ሽፈራወው ቡድነን የደቡብ ካስቴል ዋነንጫን በ3ኛ ደረጃ አጠናቋል፡፡

90+3′ ሚካኤል ለማ 3 ተጫዋቾችን አታሎ ያቀበለውን ጣጣውን የጨረሰ ኳስ ፍቃደዱ ወርቁ ሳይጠቀምበት ቀርቷል፡፡

ተጨማሪ ደቂቃ
መደበኛው የጨዋታ ክፍለ ጊዜ ተጠናቆ 4 ደቂቃ ተጨምሯል፡፡

ቢጫ ካርድ
90′ ቢንያም ሃብታሙ የማስጠንቀቂያ ካርድ ተመልክቷል፡፡

85′ ጨዋታው የተቀዛቀዘ እንቅስቃሴ እየታየበት ይገኛል፡፡

የተጫዋች ለውጥ – ኢትዮጵያ ቡና
71′
ኤልያስ ማሞና መስዑድ መሐመድ ወጥተው ሳዲቅ ሴቾ እና አማኑኤል ዮሃንስ ገብተዋል።

ቢጫ ካርድ
69′
ጋቶች ፓኖም እና ሚካኤል ለማ በፈጠሩት ውዝግብ የማስጠንቀቂያ ካርድ ተመልክተዋል፡፡

የተጫዋች ለውጥ – ቡና
62′
ኤፍሬም ወንድወሰን ወጥቶ ፍራኦል መንግስቱ ገብቷል፡፡

ቢጫ ካርድ
57′
ቢንያም አየለ የማስጠንቀቂያ ካርድ ተመልክቷል፡፡

ጎልልል!!! ቡና
56′ ከመስመር የተሻገረውን ኳስ ሳሚ ሳኑሚ በግንባሩ በመግጨት ኢትዮጵያ ቡናን ወደ ጨዋታው የመለሰች ግብ ከመረብ አሳርፏል፡፡

የተጫዋች ለውጥ – ቡና
55′
አስናቀ ሞገስ ወጥቶ ቶማስ እሸቱ ገብቷል፡፡

55′ ኢትዮጵየያ ቡና ተጭኖ ቢጫወትም የግብ እደድሎች መፍጠር አልቻለም፡፡

ተጀመረ!
2ኛው አጋማሽ የጨዋታ ክፍለ ጊዜ ተጀምሯል፡፡


picsart_1475599616679

እረፍት!!
የመጀመሪያው አጋማሽ በድሬዳዋ ከተማ 2-0 መሪነት ተጠናቋል፡፡

42′ ጋቶች ያሻገረለትን ኳስ አስቻለው ታመነ ሞክሮ በግቡ ቋሚ ለጥቂት ወጥቷል፡፡

ጎልልል!!! ድሬዳዋ ከተማ
37′ ከማዕዘን ምት የተሻገረውን ኳስ ቴድሮስ ሁሴን በግንባሩ በመግጨት አስቆጥሯል፡፡

27′ ኤልያስ ማሞ ከርቀት አክርሮ የመታውን ኳስ ቢንያም አውጥቶታል፡፡

24′ ረመዳን ከመስመር ያሻገረውን ኳስ ፍቃዱ በግንባሩ ገጭቶ ወደ ውጪ ወጥቶበታል፡፡

21′ በአንድ ሁለት ቅብብል ወደ ውስጥ በመግባት ምስጋናው ሞክሮ ዮሀሃንስ ይዞበታል፡፡

19′ ከማዕዘን የተሻማውን ኳስ ኤፍሬም ወንድወሰን ሞክሮ ወደ ውጪ ወጥቶበታል፡፡

17′ ረመዳን ያሻማውን የቅጣት ምት ኳስ ምስጋናው ወልደዮሃንስ ሞክሮ ወደ ውጪ ወጥቷል፡፡

* ድሬዳዋ ከተማ የተሻለ እንቅስቃሴ በማሳየት ላየይ ይገኛል፡፡ ወደ ቡና የግብ ክልል በተደጋጋሚ በመድረስ ላይም ይገኛሉ፡፡

15′ በሀዋሳ አለምአቀፍ ስታድየም የተገኘው ተመልካች እጅግ ጥቂት ነው፡፡

11′ አማረ በቀለ ከርቀት አክርሮ የመታው ኳስ ለጥቂት የግቡን ቋሚ ታኮ ወጥቷል፡፡

10′ ሚካኤል በግሩም ሁኔታ ለፍቃዱ ያሻገረለትን ኳስ ፍቃዱ ወደ መሃል ሲያሻማ ዮሃንስ በዛብህ ቀድሞ አድኖታል፡፡

ጎልልል!!! ድሬዳዋ
6′ ፍቃዱ ወርቁ በቀኝ መስመር ተከላካዮችን አምልጦ በግሩም አጨራረስ ድሬዳዋ ከተማን ቀዳሚ አድርጓል፡፡

ተጀመረ!
ጨዋታው በኢትዮጵያ ቡና አማካኝነት ተጀመረ፡፡


የኢትዮጵያ ቡና አሰላለፍ

28 ዮሃንስ በዛብህ

21 አስናቀ ሞገስ – 16 ኤፍሬም ወንድወሰን – 4 ኤኮ ፌቮር – 13 አህመድ ረሺድ

9 ኤልያስ ማሞ – 25 ጋቶች ፓኖም – መስኡድ መሃመድ (አምበል)

24 አስቻለው ግርማ – 20 ሳሚ ሳኑሚ – 14 እያሱ ታምሩ

ተጠባባቂዎች
1 ጆቤድ ኡመድ
19 አክሊሉ ዋለልኝ
27 ዮሴፍ ዳሙዬ
2 ፍራኦል መንግስቱ
26 አማኑኤል ዮሃንስ
12 ቶማስ እሸቱ
7 ሳዲቅ ሴቾ

የድሬዳዋ ከተማ አሰላለፍ

23 ቢንያም ሃብታሙ

2 ዘነበ ከበደ – 4 ተስፋዬ ዲባባ (አምበል) – 5 ዘሪሁን አንሼቦ – 27 አማረ በቀለ

42 ቴዎድሮስ ሁሴን – 10 ረመዳን ናስር – 99 ምስጋናው ወልደዮሃንስ – 8 ሚካኤል ለማ

19 ፍቃዱ ወርቁ – 9 ቢንያም አየለ

ተጠባባቂዎች
28 ወርቅነህ ዲባባ
20 አብዱልፈታህ ከማል
35 አልሳሃሪ አልማሃዲ
22 አብዲ መሃመድ
26 አሳምነው አንጀሎ
70 ያሬድ ታደሰ

picsart_1475599616679

Leave a Reply