አርባምንጭ ከተማ ከ ሲዳማ ቡና – ቀጥታ የፅሁፍ ስርጭት

FTአርባምንጭ ከተማ1-3ሲዳማ ቡና

15′ ወንድሜነህ ዘሪሁን | 17′ 46’90+2′ አዲስ ግደይ

         ቀጥታ የጽሁፍ ስርጭት        


ተጠናቀቀ!!!!
ሲዳማ ቡና ከመመራት ተነስቶ በአዲስ ግየይ ሐት-ትሪክ በመታገዝ 3-1 አሸንፎ የ2009 የደቡብ ካስቴል ዋንጫ አሸናፊ ሆኗል፡፡ ውድድሩን በአጠቃላይ ለ3ኛ ጊዜ በማሸነፍ ሪከርዱን መጨበጥም ችሏል፡፡

ጎልልል!!! ሲዳማ ቡና!!!
90+2′ አዲስ ግደይይይይይይ በግሩም የአክሮባቲክ ምት ሐት-ትሪክ የሰራበትን ጎል ከመረብ አሳርፏል፡፡ 

ተጨማሪ ደቂቃ
መደበኛው የጨዋታ ክፍለ ጊዜ ተጠናቆ 4 ደቂቃ ተጨምሯል፡፡

የተጫዋች ለውጥ – ሲዳማ ቡና
84′
በረከት አዲሱ ወጥቶ ዮናታን ፍስሃ ገብቷል፡፡

የተጫዋች ለውጥ – አርባምንጭ ከተማ
83′
ምንተስኖት አበራ ወጥቶ አስጨናቂ ጸጋዬ ገብቷል፡፡

78′ አዲስ ግደይ ሐት-ትሪክ ሊሰራበት የሚችልበትን እድል አግኝቶ ሳይጠቀምበት ቀርቷል፡፡

የተጫዋች ለውጥ – አርባምንጭ
76′
ወንድሜነህ ዘሪሁን ወጥቶ ታሪኩ ጎጀሌ ገብቷል፡፡

ቢጫ ካርድ
73′
ወንድሜነህ ዘሪሁን ፍጹም ተፈሪ ላይ በሰራው ጥፋት የማስጠንቀቂያ ካርድ ተመልክቷል፡፡

የተጫዋች ለውጥ – ሲዳማ ቡና
68′
ወሰኑ ማዜ ወጥቶ ሙጃይድ መሃመድ ገብቷል፡፡

የተጫዋች ለውጥ – አርባምንጭ ከተማ
66′ 
ተሾመ ታደሰ ወጥቶ ገብረሚካኤል ያዕቆብ ገብቷል፡፡

የተጫዋች ለውጥ – ሲዳማ ቡና
66′
ኤሪክ ሙራንዳ ወጥቶ ላኪ ሳኒ ገብቷል፡፡

60′ ጸጋዬ አበራ ከግብ ጠባቂው አንድ ለአንድ ተገናኝቶ የሞከረውን ኳስ ለአለም አድኖበታል፡፡ የተመለሰውን ኳስ ታደለ መንገሻ ቢሞክረውም የሲዳማ ተከላካዮች ተረባርበው አውጥተውታል፡፡

55′ አርባምንጭ ከተማዎች በኳስ ቁጥጥር ብልጫ ቢኖራቸውም የሲዳማ ቡናን የተከላካይ ክፍል ሰብረው የግብ እድሎች መፍጠር አልቻሉም፡፡

ጎልልል!!! ሲዳማ ቡና
46′ አዲስ ግደይ የአርባምንጭ ተከላካዮችን በፍጥነት አምልጦ በመግባት ሲዳማን መሪ ያደረገች ግብ ከመረብ አሳርፏል፡፡

ተጀመረ!
2ኛው አጋማሽ የጨዋታ ክፍለ ጊዜ ተጀመረ፡፡

የእረፍት ሰአት ለውጥ – አርባምንጭ
ወርቅይታደል አበበ እና ተካልኝ ደጀኔ ወጥተው ጸጋዬ አበራ እና ታገል አበበ ገብተዋል፡፡


picsart_1475599616679

እረፍት!!!
የመጀመርያው አጋማሽ የጨዋታ ክፍለ ጊዜ በአቻ ውጤት ተጠናቋል፡፡

ተጨማሪ ደቂቃ
የመጀመሪያው አጋማሽ መደበኛ ክፍለ ጊዜ ተጠናቆ 2 ደቂቃ ተጨምሯል፡፡

40′ በአርባምንጭ በኩል ተመስገን ካስትሮ ፤ በሲዳማ በኩል ትርታዬ ደመቀ እና አበበ ጥላሁን የቀድሞ ክለባቸውን በተቃራኒው በመግጠም ላይ ይገኛሉ፡፡

ቢጫ ካርድ
35′
ተመስገን ካስትሮ በወሰኑ ማዜ ላይ በሰራው ጥፋት የማስጠንቀቂያ ካርደድ ተመልክቷል፡፡

33′ የሲዳማ ቡና የኋላ መስመር የመናበብ ችግሮች እየታዩበት ይገኛል፡፡

ቢጫ ካርድ
29′
አመለ ሚልኪያስ የማስጠንቀቂያ ካርድ ተመልክቷል፡፡

20′ ጨዋታው በሞቀ ድባብ በመካሄድ ላይ ይገኛል፡፡ በሁለቱም በኩል ጥሩ እንቅስቃሴ እየተደረገም ይገኛል፡፡ የስታድየሙ የተመልካች ቁጥር እየጨመረ ሲሆን የሲዳማ ደጋፊዎች በግራ ፤ የአርባምንጭ ደጋፊዎች በቀኝ አቅጣጫ ተቀምጠው ለቡድናቸው ድጋፍ እየሰጡ ይገኛሉ፡፡

ጎልልል!!! ሲዳማ ቡና
17′ አዲስ ግደይ ከመሃል ሜዳ የተሻገረለትን ኳስ በምርጥ አጨራረስ ወደ ግብነት ቀይሮታል፡፡ ግሩም የኳስ ቁጥጥር! ግሩም አጨራስ!

ጎልልል!!! አርባምንጭ
15′ ተሾመ ታደሰ ያመቻቸለትን ኳስ ተጠቅሞ ወንድሜነህ ዘሪሁን አርባምንጭን ቀዳሚ አድርጓል፡፡

13′ አዲስ ግደይ ከግቡ የግራ መስመር የሞከረው ኳስ የውጪኛውን መረብ መትቶ ወጥቷል፡፡

5′ ሙራንዳ ከመስመር የተሻገረውን ኳስ ተጠቅሞ የሞከረው ኳስ ወደ ውጨጪ ወጥቷል፡፡

ተጀመረ!!!
ጨዋታው በሲዳማ ቡና አማካኝነት ተጀምሯል፡፡

09:15 የእለቱ የክብር እንግዶች ተጫዋቾችን በመተዋወቅ ላይ ይገኛሉ፡፡


የአርባምንጭ ከተማ አሰላለፍ 

1 አንተነህ መሳ

2 ወርቅይታደል አበበ – 13 ወንድወሰን ሚልኪያስ – 9 ተመስገን ካስትሮ – 14 ተካልኝ ደጀኔ

4 ምንተስኖት አበራ – 8 አማኑኤል ጎበና (አምበል) – 10 ወንድሜነህ ዘሪሁን – 17 ታደለ መንገሻ

23 ተሾመ ታደሰ – 12 አመለ ሚልኪያስ

ተጠባባቂዎች

71 ጃክሰን ፊጣ

3 ታገል አበበ

18 ጸጋዬ አበራ

16 በረከት ቦጋለ

21 አስጨናቂ ጸጋዬ

19 ገብረሚካኤል ያዕቆብ

6 ታሪኩ ጎጀሌ


የሲዳማ ቡና አሰላለፍ

24 ለአለም ብርሃኑ (አምበል)

3 ግሩም አሰፋ – 16 አበበ ጥላሁን – 4 አንተነህ ተስፋዬ – 22 ወሰኑ ማዜ

14 አዲስ ግደይ – 5 ፍጹም ተፈሪ – 20 ሙሉአለም መስፍን – 6 ትርታዬ ደመቀ

13 ኤሪክ ሙራንዳ – 9 በረከት አዲሱ

ተጠባባቂዎች

33 መሳይ አያኖ

23 ሰንዴይ ሙቱኩ

18 ሙጃይድ መሃመድ

19 አዲስአለም ደበበ

7 ከማል አቶም

11 ዮናታን ፍስሃ

27 ላኪ ሳኒ

picsart_1475599616679

Leave a Reply