የአዲስ አበባ ከተማ ዋንጫ – ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከ ኢትዮጵያ ቡና

ከደረጃ ጨዋታም በላይ

የአዲስ አበባ ከተማ ዋንጫ በደረጃ ጨዋታ ዛሬ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እና ኢትዮጵያ ቡናን ያገናኛል፡፡ በግማሽ ፍፃሜው በኢትዮጵያ መድን ሳይጠበቅ ሽንፈት የደረሰበት የአሰልጣኝ ፀጋዬ ኪዳነማርያም ንግድ ባንክ እና በቅዱስ ጊዮርጊስ ከባድ ሽንፈትን ያስተናገዱት የጳውሎስ ጌታቸው ቡና የዛሬ 10 ሰአቱን ጨዋታ ከሽንፈታቸው ለማገገም ይጠቀሙበታል፡፡ ጨዋታው ያን ያህል ወሳኝ ባይሆንም የእለቱ ገቢ 70 በመቶ ለጋዜጠኛ መኳንንት በርሄ ህክምና ድጋፍ የሚውል በመሆኑ አላማው ትልቅ ነው፡፡

የደረጃ ጨዋታው ከመከናወኑ ቀደም ብሎ በ8 ሰአት ለጋዜጠኛ መኳንንት በርሄ ድጋፍ በሚውል የወዳጅነት ጨዋታ በሰሜን አሜሪካ የሚገኙ የቀድሞ ተጫዋቾች ከ ጋዜጠኞች ጋር ጨዋታ ያደርጋሉ፡፡ የቀድሞዎቹ ተጫዋቾች ለዚህ በጎ አላማ ጉዟቸውን ሳይቀር የሰረዙ ሲሆን ተመልካቹም በብዛት ስቴድየም በመገኘት የጋዜጠኛውን ህይወት ይታደጋል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

{jcomments on}

ያጋሩ