የግሎ ካፍ የአፍሪካ የዓመቱ ምርጥ ተጫዋች ዕጩዎች ይፋ ሆነዋል

በየአመቱ አስደናቂ ብቃት እና ስኬት ለሚያስመዘግቡ አፍሪካዊያን ተጫዋቾች የሚሰጠው ሽልማት በናይጄሪያ ይካሄዳል፡፡

ግሎ በተባለው ድርጅት ስፖንሰር የተደረገው ሽልማቱ የአመቱ የአፍሪካ ኮከብ ተጫዋች እና በአፍሪካ ሊጎች ውስጥ የሚጫወት ኮከብ ተጫዋች በሚል ሁለት ዘርፍ ካፍ ሽልማት ሲሰጥ ቆይቷል፡፡ ካፍ ባሳለፍነው ሳምንት መጨረሻ ዕጩዎችን ይፋ ያደረገ ሲሆን በአመቱ የአፍሪካ ኮከብ ተጫዋች ዝርዝር ውስጥ 30 እንዲሁም በአፍሪካ ሊጎች ውስጥ የሚጫወት ኮከብ ተጫዋች ውስጥ 25 ተጫዋቾች ተካትተዋል፡፡
የእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ የ2015/16 የውድድር ዘመን ኮከብ ተጫዋቾች አልጄሪያዊው ሪያድ ማህሬዝ ከሃገሩ ልጆች ኢስላም ስሊማኒ እና ኤል አረብ ሂላል ሱዳኒ ጋር በእጩነት ቀርቧል፡፡ የአምና አሸናፊው ፔር ኤምሪክ ኦባምያንግ ክብሩን ዳግመኛ ለማግኘት አሁንም በዝርዝሩ ውስጥ ይገኛል፡፡ በሮማ እና በግብፅ ብሄራዊ ቡደን ተስፋ ሰጪ እንቅስቃሴ ያሳየው መሃመድ ሳላ ሌላኛው በዕጩ ውስጥ የተካተተ ተጫዋች ነው፡፡ ከምስራቅ አፍሪካ ዩጋንዳዊው የቀድሞ የቅዱስ ጊዮርጊስ ግብ ጠባቂ ዴኒስ ኦኒያንጎ፣ የዓምና በአፍሪካ ውስጥ የሚጫወት የአፍሪካ የዓመቱ ምርጥ ተጫዋች አሸናፊ ታንዛኒያዊው ማባውና ሳማታ እና የቶትናሃሙ ኬንያዊ አማካይ ቪክቶር ዋኒያማ መካተት ችሏል፡፡ ማሜሎዲ ሰንዳውንስ ለቻምፒየንስ ሊጉ ፍፃሜ ማብቃት የቻለው ኦኒያንጎ ከክለብ አጋሮቹ ካማ ቢሊያት እና ኪገን ዶሊ ጋር በሁለቱም ዘርፍ ዕጩ ውስጥ መግባት ችለዋል፡፡ በማንችስተር ሲቲ የተሳካ ግዜን እያሳለፈ የሚገኘው ናይጄሪያዊው ኬሌቺ ኢያናቾ፣ የሊቨርፑሉ ሰይዴ ማኔ፣ ሳሙኤል ኤቶ፣ ኤሪክ ቤሊ፣ መሀዲ ቤናቲያ፣ ለቪያሪያል እና ዲ.ሪ. ኮንጎ ድንቅ ብቃቱን ያሳየው ሲድሪክ ባካምቡ፣ የካሜሮኑ ቤንጃሚን ሙካንጆ፣ የቱኒዚያዎቹ ወሃቢ ካዝሪ እና አይመን በአብድኑር እንዲሁም የናይጄሪያው አህመድ ሙሳ በእጩ ዝርዝር ውስጥ ይገኙበታል፡፡

glo-caf-awards-484x336


በአፍሪካ ውስጥ የሚጫወቱ ዝርዝር ውስጥ የዛማሌኮቹ አሊ ጋብር፣ አይመን ሃፍኒ እና ባሰም ሞርሲ መካተት ችለዋል፡፡ ቲፒ ማዜምቤን ለኮንፌድሬሽን ካፕ ፍፃሜ ያበቁት ሳሊፍ ኩሊባሊ እን ሬንፎርድ ካላባ ሲካተቱ ላይቤሪያዊው ዊሊያም ጄቦር ባልተጠበቀ መልኩ ልክ እንደ ኦኒያንጎ ሁሉ በሁለቱም ዘርፍ በእጩነት መቅረብ ችሏል፡፡ ፋብሪስ ኦንዳማ፣ ሃምዛ ላሃማር፣ ጄሲ ዌሬ፣ ሞርጋን ቤቶራንጋል ፣ የሰንዳውንስ የመሃል ሜዳ ተጫዋች ሆሎምፖ ኬኬና እና ቺሶማ ቺካታራ ሌሎች የሚጠቀሱ ተጫዋቾች ናቸው፡፡
በዕጩዎች ዝርዝር ላይ ካፍ የተተቸ ሲሆን መካተት ያልነበረባቸው ተጫዋቾች ተካትተው በጥሩ ብቃት ላይ የሚገኙ መዘለላቸው ብዙዎችን አስገርሟል፡፡ በፖርቹጋሉ ሪዮ አቬ የወረደ አቋም ካሳየ በኃላ በክረምቱ ወር ዋይዳድ ካዛብላንካን የተቀላቀለው የአጥቂው ዊልያም ጄቦር በሁለቱም ዘርፍ መታጨት ብዙዎችን አስገርሟል፡፡ ጄቦር በሞሮኮ ቦቶላ ሊግ አንድ እንዲሁም በቻምፒየንስ ሊግ አንድ ግብ ማስቆጠር ቢችልም የካዛብላንካውን ክለብ የተቀላቀለው በቅርብ ነው፡፡ የደቡብ አፍሪካ ግብ ጠባቂ ኡቱሚሌግ ኩኔ፣ የዲ.ሪ. ኮንጎው ጆይስ ሎማሊሳ እና የናይጄሪያው ቺሶማ ቺካታራ መካተት ጥያቄ አስነስቷል፡፡ ሎማሊሳ በውድድር ዓመቱ ለቪታ ክለብ እምብዛም መሰለፍ አልቻለም፡፡ ቺካታራ ደግሞ ከቻን 2016 መጠናቅ በኃላ በክለቡ እና በዋይዳድ ካዛብላንካ መካከል በዝውውር ምክንያት በተነሳው እሰጣ ገባ በቂ የመጫወት እድልን አላገኘም፡፡ የካፍ ኮንፌድሬሽን ካፕ የፍፃሜ ተፋላሚው ኤምኦ ቤጃያ አንድ ተጫዋችን በዝርዝሩ ውስጥ መካተቱም ለቡዙዎች አልተዋጠላቸውም፡፡ የብራጋ እና የፈርኦኖቹ የፊት መስመር ተሰላፊ አህመድ ሃሰን ኩካ እና በዜስኮ ዩናይትድ ቻምፒየንስ ሊግ የግማሽ ፍፃሜ መድረስ ላይ ትልቅ ሚና የነበረው ክሎተስ ቻማ ከዕጩዎቹ ተዘሏል፡፡

የአመቱ የአፍሪካ ምርጥ ተጫዋች ዘርፍ በአውሮፓ የሚጫወቱ ተጫዋቾች ስር ቁጥጥር ውስጥ ገብቷል፡፡ በ2015 የሱዳኑ ሙዳሂቲር ካሬካ 10ሩ ውስጥ ከመግባቱ በስተቀር በአብዛኛው በአውሮፓ የሚጫወቱ ተጫዋቾች ለሽልማቱ ቅድሚያውን ያገኛሉ፡፡

 

የግሎ ካፍ የ2016 የአፍሪካ የዓመቱ ምርጥ ተጫዋች የእጩዎች ዝርዝር

screenshot_2016-10-17-15-52-01የግሎ ካፍ የ2016 በአፍሪካ ውስጥ የሚጫወት የዓመቱ ምርጥ ተጫዋች የእጩዎች ዝርዝር

 

based-in-africa

 

Leave a Reply