የአዲስ አበባ እግርኳስ ፌዴሬሽን የሚያዘጋጀው አመታዊው የአዲስ አበባ ከተማ ዋንጫ በመጪው ቅዳሜ ጥቅምት 12 እንደሚጀምር ፌዴሬሽኑ አስታውቋል፡፡ ፌዴሬሽኑ የውድድሩን መጀመርያ ቀን ይፋ ከማድረጉ ውጪ የጨዋታዎቹን ቀን እና ሰአት አልገለጸም፡፡
ከመስከረም 28 ጀምሮ ሊካሄድ ቀን ተቆርጦለት የነበረው ይህ ውድድር በሃገሪቱ በነበረው አለመረጋጋት እና ምክንያት ላልተወሰ ጊዜ ተራዝሞ ቆይቷል፡፡
በውድድሩ ላይ 7 ክለቦች የሚሳተፉ ሲሆን የዩጋንዳው ኬሲሲኤ ወደ አዲስ አበባ የማይመጣ መሆኑ ታውቋል፡፡
ከ3 ሳምንታት በፊት የወጣው የውድድሩ የምድብ ድልድል ይህንን ይመስላል፡-
ምድብ ሀ : ኢትዮ ኤሌክትሪክ ፣ መከላከያ ፣ ቅዱስ ጊዮርጊስ ሲደለደሉ
ምድብ ለ : ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፣ ደደቢት ፣ አዳማ ከተማ ፣ አዲስ አበባ ከተማ