ጅማ አባቡና የአዲስ አበባ ከተማ ዋንጫ ላይ ይሳተፋል

አዲሱ የፕሪሚየር ሊግ ክለብ ጅማ አባቡና በመጪው ቅዳሜ በሚጀመረው የአዲስ አበባ ከተማ ዋንጫ ላይ እንደሚካፈል ፌዴሬሽኑ አስታውቋል፡፡

በውድድሩ ላይ በተጋባዥነት ይሳተፋል ተብሎ የነበረው ኬሲሲኤ ሳይመጣ በመቅረቱ የዘንድሮው ውድድር በ7 ክለቦች መካከል ይካሄዳል ተብሎ ቢጠበቅም በመጨረሻ በተደረገው ጥረት ጅማ አባ ቡና ተሳታፊ እንዲሆን ተደርጓል፡፡

ጅማ አባ ቡና መካተቱኅ ተከትሎ ምድብ 1 ላይ በኬሲሲኤ ቦታ የተመደበ ሲሆን በመጪው ቅዳሜ በሚደረገው የመክፈቻ ጨዋታ ከመከላከያ ጋር 08:00 ላይ የሚጫወት ይሆናል፡፡ 10:00 ላይ ደግሞ ቅዱስ ጊዮርጊስ ከ ኢትዮ ኤሌክትሪክ ይገናኛሉ፡፡

Leave a Reply