የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የ2009 የውድድር ዘመን ለ3ኛ ጊዜ ተራዝሞ ህዳር 3 እንዲጀምር ተወስኗል፡፡
የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን ትላንት ባደረገው ውይይት ከሃገሪቱ ወቅታዊ ሁኔታ ምክንያት የፕሪሚየር ሊጉ የመጀመርያ ቀን ከጥቅምት 20 ወደ ህዳር 3 እንዱሸጋገር ተወስኗል፡፡ ከዚህ ቀደም መስከረም 28 እንዲጀመር ተወስኖ የነበረው ሊጉ በክለቦች ጥያቄ መሰረት ወደ ጥቅምት 20 መሸጋገሩ የሚታወስ ነው፡፡
አዲሱን የቀን ማሻሻያ ተከትሎ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ እና ከፍተና ሊግ በተመሳሳይ ቀን የሚጀመሩ ይሆናል፡፡
ለማስታወስ ያህል የመጀመርያው ሳምንት ጨዋታዎች እነዚህን ይመስላሉ፡-
ቅዱስ ጊዮርጊስ ከ አርባምንጭ ከተማ
ሲዳማ ቡና ከ ፋሲል ከተማ
ኢትዮጵያ ቡና ከ ደደቢት
ወላይታ ድቻ ከ መከላከያ
ሀዋሳ ከተማ ከ አዲስ አበባ ከተማ
ጅማ አባ ቡና ከ ኢትዮ ኤሌክትሪክ
ወልድያ ከ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ
አዳማ ከተማ ከ ድሬዳዋ ከተማ
የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 1ኛ ዙር ሙሉ ፕሮግራም