የአዲስ አበባ ከተማ ዋንጫ ዛሬ ሲጀመር ቅዱስ ጊዮርጊስ አሸንፏል

የ2009 የአዲስ አበባ ከተማ ዋንጫ ዛሬ በይፋ ተጀምሯል፡፡ የምድብ ሀ 2 ጨዋታዎች ተስተናግደው ጅማ አባ ቡና እና መከላከያ ነጥብ የተጋሩበትን ፣ ቅዱስ ጊዮርጊስ 3 ነጥብ ያስመዘገበበትን ድል አስመዝግበዋል፡፡
08፡30 ላይ ጅማ አባ ቡና ከ መከላኬ ያደረጉት ጨዋታ ያለ ግብ በአቻ ውጤት ተጠናቋል፡፡ በጨዋታው አዲሱ የፕሪሚየር ሊግ ክለብ ጅማ አባ ቡና የተሸለ እንቅስቃሴ ያሳ ሲሆን የግብ እድሎችን በመፍጠር ረገድም ከጦሩ የተሻለ ነበር፡፡
10፡30 ላይ ቅዱስ ጊዮርጊስ ከ ኢትዮ-ኤሌክትሪክ ያደረጉት ጨዋታ በፈረሰኞቹ የበላይነት ተጠናቋል፡፡ አቡበከር ሳኒ በ7ኛው ደቂቃ ባስቆጠረው ግብ ቅዱስ ጊዮርጊስን ቀዳሚ ሲያደርግ አዲስ ነጋሽ በ28ኛው ደቂቃ የተገኘችውን የፍፁም ቅጣት ምት ወደ ግብነት ቀይሮ ኤሌክትሪክን አቻ አድርጓል፡፡ የመጀመርያው አጋማሽ መደበኛ ክፍለ ጊዜ ተጠናቆ በተጨማሪዎቹ ደቂቃዎች አቡበከር ሳኒ እና ራምኬል ሎክ የቅዱስ ጊዮርጊስን መሪነት ወደ 3-1 ሲያሰፉ ከእረፍት መልስ በ48ኛው ደቂቃ ራምኬል ሎክ የማሳረጊያውን ግብ አስቆጥሯል፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ ዋንጫ ነገ በሚደረጉ የምድብ ለ ጨዋታዎች ሲቀጥል 08፡00 ላይ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከ አዲስ አበባ ከተማ ፣ 10፡00 ደደቢት ከ አዳማ ከተማ በአዲስ አበባ ስታድየም ይጫወታሉ፡፡

img_2008

1 Comment

Leave a Reply