በአአ ከተማ ዋንጫ ሁለተኛ ቀን ውሎ ንግድ ባንክ እና አዳማ አሸንፈዋል

ትላንት የተጀመረው የአዲስ አበባ ከተማ ዋንጫ የምድብ ለ ጨዋታዎች ዛሬ ተካሂደው ንግድ ባንክ እና አዳማ ከተማ አሸንፈዋል፡፡

08:00 ላይ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አዲስ አበባ ከተማን ገጥሞ በአዲሱ ፈራሚ ፒተር ኑዋዲኬ የ10ኛ ደቂቃ ግብ 1-0 አሸንፏል፡፡ በጨዋታው የፕሪሚየር ሊጉ እንግዳ አአ ከተማ የኳስ ቁጥጥር እና የግብ ሙከራ የበላይነት ቢኖረውም በጨወታው መጀመርያ የተቆጠረችውን ግብ መቀልበስ ሳይችሉ ቀርተዋል፡፡

picsart_1477370306882

10:00 ላይ ተጋባዡ አዳማ ከተማ ደደቢት ላይ ሙሉ የበላይነት በመውሰድ 3-0 አሸንፏል፡፡ ደደቢት አመዛኞቹን ቋሚ ተሰላፊዎችን ያልተጠቀመ ሲሆን አዳማ በአንጻሩ የተሟላ ቡድኑን ይዞ ቀርቧል፡፡

የአዳማን የድል ግቦቸች ከእረፍት በፊት ከመረብ ያሳረፉት ጥላሁን ወልዴ ፣ ሱራፌል ዳኛቸው እና ፋሲካ አስፋው ናቸው፡፡

ውድድሩ የ1 ቀን እረፍት በማድረግ ማክሰኞ ሲቀጥል ከምድብ ሀ 09:00 ላይ ቅዱስ ጊዮርጊስ ከ ጅማ አባ ቡና ፤ 11:00 ላይ ኢትዮ-ኤሌክትሪክ ከ መከላከያ ይጫወታሉ፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *