የዳሸን ቢራው ተከላካይ አይናለም ኃይሉ ዛሬ ከሊግ ስፖርት ጋዜጣ ጋር ባደረገው ቃለምልልስ ከጋዜጠኞች ስለሚደርስበት ግፊት ፣ ስለ ክለቡ እና ስለ መጪ የእግር ኳስ ህይወቱ ተናግሯል፡፡ሙሉውን ቃለ ምልልስ ከጋዜጣው እንድታነቡ እየጋበዝን በቃለ ምልልሱ ከተናገራቸው ውስጥ አንኳር አንኳሩን መርጠን አቅርበንላችኋል፡፡
ስለ ጋዜጠኞች
በብሄራዊ ቡድን ውስጥ ያጣጣምናቸው ስኬቶች እንዲገኙ ሚድያው የበኩሉን ጥረት አድርጓል፡፡ በህዝብ ዘንድ ሞገስ እነዲኖረንም አድርገውናል፡፡ በቻን በተመዘገበው ውጤት በሚድያዎች የቀረበው ትችት ግን ከልክ ያለፈ ነው፡፡ አንድን ዘገባ ወደ ህዝብ ከማድረሳቸው በፊት ትርፍ እና ኪሳራውን ማመዛዘን ይኖርባቸዋል፡፡
ሚድያዎች በኛ ላይ ያላቸውን ጥላቻ አውቃለሁ፡፡እነሱ ለኛ ያለቸውን ጥላቻ ያህል እኔም እጠላቸዋለሁ
ከብሄራዊ ቡድን ራሱን አገለለ ስለመባሉ
በቦታዬ ብቃት ያለው ተሰላፊ ከመጣ ለማስረከብ ዝግጁ ነኝ ፡፡ ቦታውን ለዘላለም ልይዘው አልችልም፡፡
ስለ ዳሸን ቢራ
ቡድኑ እስካሁን ግብ አለማስቆጠሩ አያሳስበኝም ፡፡ በቅርቡ በሚከፈተው የዝውውር መስኮት ሁለት አጥቂዎችን ካስፈረምን ችግራችን ይቀረፋል፡፡ ከውጪ አጥቂ ለማስፈረምም ክለባችን ግንኙነት ጀምሯል፡፡
ስለ እድሜ
አሁን 27 አመቴ ነው ፡፡ ይህም ትክክለኛ እድሜዬ ነው፡፡ ነገር ግን በእድሜ ዙርያ በሚድያዎች የሚወራው ነገር ጫና ውስጥ ከቶናል፡፡
ስለ ቀጣይ እግርኳስ ህይወቱ
ለቀጣዮቹ 10 አመታት በብቃት የመጫወት አቅም አለኝ ፡፡ ነገር ግን ያን ያህል አመት መጫወት ፍላጎት ይኑረኝ አይኑረኝ እርግጠኛ አይደለሁም፡፡ እርግጠኛ ሆኜ የምናገረው ከዳሸን ጋር ያለኝን የ2 አመት ኮንትራት እንደማከብር ነው፡፡
ስለ ቡድን አባላቱ
ሁሉም የብሄራዊ ቡድን አባላት በሜዳም ከሜዳም ውጪ ስህተት ይሰራሉ፡፡ በቡድኑ ውስጥ የተዋቀረ ኮሚቴ በመኖሩ ችግሮች ሲፈጠሩ ወደ ውጪ ሳይወጡ እዛው መፍትሄ እናበጅለታለን፡፡
በብሄራዊ ቡድን ውስጥ አይነኬ ተጫዋቾች አሉ፡፡ ሳላዲን ሰክሮ ቢመጣ አላሰልፈውም ማለት አትችልም፡፡