አዲስ ቻምበር የአአ ከተማ ስፓንሰር ሆነ

አዲሱ የፕሪሚየር ሊግ ክለብ አዲስ አበባ ከተማ ከአዲስ አበባ ንግድ እና የዘርፍ ማህበራት ምክርቤት ጋር የስፖንሰርሺፕ ውል ተፈራርሟል፡፡ ትላንት በሂልተን አዲስ በተካሄደው ስነስርአት ከስፖንሰርሺፑ ውል በተጨማሪ የሽልማት ስነስርአት ተካሂዷል፡፡

የፋይናንስ ጥገኝነቱን ለመቅረፍ ቅዷል

በውሉ ዝረዝር ላይ ማብራርያ የሰጡት የክለቡ የቦርድ ሰብሳቢ አቶ አሰግድ ጌታቸው ከአዲስ ቻምበር ጋር የፈጠሩት ስምምነት ክለቡን ህዝባዊ መሰረት እንዲኖረው እና በገቢ በማጠናከር ከፋይናንስ ጥገኝነት ለማላቀቅ አስተዋፅኦ እንደሚኖረው ተናግረዋል፡፡

ክለቡን ወደ ፕሪሚየር ሊግ ላሳደጉ አባላት ሽልማት ተሰጥቷል

በ2008 ከፍተኛ ሊግ 3ኛ ደረጃ እና የስፖርታዊ ጨዋነት ሽልማት አሸናፊ ለሆነው ቡድን የማበረታቻ ሽልማት ተበርክቷል፡፡ ተጫዋቾች እንዳበረከቱት አስተዋጽኦ በየደረጃው ከ70-5 ሺህ ብር የተበረከተላቸው ሲሆን ለአሰልጣን ቡድኑም እንደየደረጃቸው ከ75እስከ 20 ሺህ ብር ተበርክቶላቸዋል፡፡

አዲስ አበባ ከተማ የተቆረቆረችበትን 125ና አመት በማስመልከት የተቋቋመው ክለቡ 5ኛ አመቱን ኬክ በመቁረስ ያከበረ ሲሆን ለከተማው ምክትልከንቲባ ፣ ለክለቡ ቦርድ ሰብሳቢ እና ለአዲስ ቻምበር ቦርድ ፕሬዝዳንት የመጀመርያዎቹ 3 የደጋፊነት መታወቂያዎች ተበርክተዋል፡፡

Leave a Reply