ሰሜን ሸዋ ደብረብርሃን በከፍተኛ ሊጉ ይቆያል

በኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ ላይ ከሚካፈሉት ክለቦች መካከል ዳሽን ቢራ እና ሙገር ሲሚንቶ በመፍረሳቸው በምትካቸው የሚካፈሉት ክለቦች ታውቀዋል፡፡

ዳሽን ቢራ ቀደም ብሎ መፍረሱ የተረጋገጠ በመሆኑ በፌዴሬሽኑ ደንብ መሰረት የተሻለ ነጥብ ይዞ የወረደው አክሱም ከተማ የተተካተ ሲሆን የሙገር መፍረስ በይፋ የታወቀበት ቀን በመዘግየቱ በከፍተኛ ሊጉ የእጣ ድልድል ላይ ተካቷል፡፡ አሁን የሙገር መፍረስ በመረጋገጡ ፌዴሬሽኑ በተመሳሳይ ምድብ ላይ የነበረው ሰሜን ሸዋ ደብረብርሃን እንዲካተት አድርጓል፡፡

ሰሜንሸዋ ደብረብርሃን ባለፈው የውድድር ዘመን የደብረማርቆስ ዩኒቨርሲቲን መፍረስ ተከትሎ በምትኩ ከብሄራዊ ሊግ ወደ ከፍተኛ እንዲያልፍ መደረጉ የሚታወስ ነው፡፡

Leave a Reply