የኢትዮጵያ ብሄራዊ ሊግ ህዳር 18 ይጀምራል

የኢትዮጵያ ብሄራዊ ሊግ የ2009 የውድድር ዘመን የእጣ ማውጣት ስነስርአት ዛሬ በካፒታል ሆቴል እና ስፓ ተካሂዷል፡፡ በእለቱ የ2008 ውድድር ሪፖርት የቀረበ ሲሆን የውድድር ደንብ እና ተያያዥ ጉዳዮች ቀርበው ውይይት ተደርጎባቸዋል፡፡

ዋና ዋና ነጥቦች

– በ5 ምድቦች ተከፍሏል

ከዚህ ቀደም በ7 ዞኖተት ተከፍሎ ሲካሄድ የነበረው የውድድር አሰራር ተቀይሮ በ5 ምድቦች የተከፋፈለ ሲሆን ሁሉም ምድቦች የተመጣጠነ ተሳታፊ ቁጥር እንዲኖራቸው ተደርጓል፡፡

ምድቦቹ የሚከተሉት ናቸው፡-

ምድብ 1

ወሊሶ ከተማ ፣ ቱሉ ቦሎ ከተማ ፣ ጋምቤላ ከተማ ፣ ቦሌ ክ/ከተማ ፣ ልደታ ክ/ከተማ ፣ አምቦ ከተማ ፣ ዩኒቲ ጋምቤላ ፣ አሶሳ ከተማ ፣ ሆለታ ከተማ ፣ መቱ ከተማ

ምድብ 2

ዱከም ከተማ ፣ መተሃራ ስኳር ፣ ካሊ ጅግጅጋ ፣ ቢሾፍቱ ከተማ ፣ ሐረር ሲቲ ፣ መቂ ከተማ ፣ ሞጆ ከተማ ፣ ኢትዮ ሶማሌ ልዩ ፖሊስ ፣ ወለንጪቲ ከተማ ፣ ባቱ ከተማ ፣ ቢሾፍቱ አውቶሞቲቭ ፣ ወንጂ ስኳር

ምድብ 3

ዋልታ ፖሊስ ፣ ዳባት ከተማ ፣ ደሴ ከተማ ፣ ደባርቅ ከተማ ፣ ሶሎዳ አድዋ ፣ አማራ ፖሊስ ፣ ራያ አዘቦ ፣ አዊ እምፒልታቅ ፣ አምባ ጊዮርጊስ ፣ ላስታ ላሊበላ ፣ ትግራይ ውሃ ስራ ፣ ዳሞት ከተማ

ምድብ 4

ጨፌ ዶንሳ ፣ ገላን ከተማ ፣ ተጂ ከተማ ፣ አዲስ ከተማ ክ/ከተማ ፣ ቂርቆስ ክ/ከተማ ፣ የካ ክ/ከተማ ፣ ቦሌ ገርጂ ዩኒየን ፣ ንፋስ ስልክ ላፍቶ ክ/ከተማ ፣ ጎጃም ደብረማርቆስ ፣ አአ ዩኒቨርሲቲ ፣ ለገጣፎ 01

ምድብ 5

ሚዛን አማን ፣ ጨንቻ ከተማ ፣ ቡታጅራ ከተማ ፣ ጋርዱላ ከተማ ፣ ወላይቲ ሶዶ ፣ አምበሪቾ ፣ ሮቤ ከተማ ፣ ኮንሶ ኒውዮርክ ፣ ጎባ ከተማ ፣ ቡሌ ሆራ ፣ ጎፋ ባሪንቼ ፣ ሀዲያ ሌሞ

img_1gg030

– የቀድሞው አሰራር ተቀይሯል

በዚህ የውድድር ዘመን ወደ ከብሄራዊ ሊጉ 6 ክለቦች ወደ ከፍተኛ ሊግ ያድጋሉ፡፡ ከ5 ምድቦች 1ኛ ደረጃ ይዘው የሚያጠናቅቁ እና 1 በጥሩ ሁለተኛነት የሚያጠናቅቅ ክለብ ወደ ከፍተኛ ሊጉ የሚያልፉ ይሆናል፡፡ ከዚህ ቀደም የሚያድጉ ክለቦችን ለመለየት የሚደረገው የማጠቃለያ ውድድር ዘንድሮ የማይኖር ሲሆን ወደ ከፍተኛ ሊጉ የሚያድጉት 6 ክለቦች ለደረጃ እርስ በእርስ ይጫወታሉ፡፡

– የውድድሩ መጀመርያ ቀናት ተራዝሟል

ህዳር 11 ሊጀመር ታቅዶ የነበረው ውድድሩ በአንድ ሳምንት ተራዝሞ ህዳር 18 እንዲጀምር ተወስኗል፡፡ በዚህም መሰረት የከፍተኛ ሊግ እና ብሄራዊ ሊግ በተመሳሳይ ወቅቶች የሚጀምሩ ይሆናል፡፡

– አበበ ቢቂላ ስታድየም ውድድር ላይካሄድ ይችላል

የአበበ ቢቂላ ስታድየም ዘንድሮ እድሳት ሊደረግለት የታሰበ ሲሆን በስታድየሙ የሚደረጉ ጨዋታዎች ቁጥር ሊገደብ ይችላል ተብሏል፡፡ በዚህም መሰረት ቄራ ሜዳ ፣ 22 ሜዳ ፣ ሃያት ሜዳ እና መቻሬ ሜዳ እንደአማራጭ ሜዳነት ተይዘዋል፡፡

 

2 Comments

  1. አብርሽ
    ሁሉም የመጀመሪያ ጫወታዎች መረጃ ብትገልፅልን ምን ይመስልሀል

Leave a Reply