ኢትዮጵያ ለሞሮኮው የአፍሪካ ዋንጫ ማጣርያ በቀጥታ ምድብ ማጣርያ ውስጥ ተካተተች

በ2013 የአፍሪካ ዋንጫ የተሳተፈችው ኢትዮጵያ ወደ 2015 የአፍሪካ ዋንጫ ለማለፍ በሚደረገው የማጣርያ ውድድር ካለ ቅድመ ማጣርያ ምድብ ውስጥ ተካታለች፡፡ ካፍ ባወጣው ድልድል መሰረት ኢትዮጵያን ጨምሮ 21 ሃገራት ምድቡን ተቀላቅለዋል፡፡

የቅርብ ጊዜ ውጤቶችን ተንተርሶ ካፍ ባወጣው ደረጃ መሰረት ኢትዮጵያ 16ኛ ደረጃን መያዟ በቀጥታ ወደ ምድብ ማጣርያው ለመግባት አግዟታል፡፡

በቻን ኢትዮጵያን ያሸነፉት ኮንጎ ብራዛቪል እና ሊቢያን ጨምሮ 29 ሃገራት በቅድመ ማጣርያ ወደ ምድብ ድልድሉ ይገባሉ፡፡ በቅድመ ማጣርያው የሚያልፉ 7 ሃገራት 21ዱን ሃገራት ተቀላቅለው በ7 ምድብ የሚከፈሉ ሲሆን አፕሪል 27 ቀን 2014 ካይሮ በሚገኘው የካፍ ፅህፈት ቤት የምድብ ማጣርያ ድልድሉ እጣ ይወጣል፡፡

በተያያዘ ዜና የአፍሪካ እግርኳስ ኮንፌድሬሽን (ካፍ) የ2019 እና 2021 የአፍሪካ ዋንጫን ለማስተናገድ ጥያቄ ያቀረቡት ሃገሮችን መርምሮ የመጨረሻ እጩዎችን አሳውቋል፡፡ ከሁለቱ የአፍሪካ ዋንጫዎች ንዱን ለማስተናገድ ሃሳብ የነበራት ኢትዮጵያም በመጨረሻው ዝርዝር ውስጥ ሳትካተት ቀርታለች፡፡

ካፍ ባሳወቀው የመጨረሻ ዝርዝር ውስጥ የተካተቱት ሃገሮች የሚከተሉት ናቸው፡፡

ለ2019 – አልጄርያ ፣ ካሜሩን ፣ ኮትዲቯር ፣ ዲሞክራቲክ ሪፑብሊክ ኮንጎ እና ዛምቢያ

ለ2021 – አልጄርያ ፣ ኮትዲቯር ፣ጊኒ

{jcomments on}

ያጋሩ