ሀዋሳ ከተማ የሁለት የውጭ ዜጎችን ለማስፈረም ተቃርቧል

ሀዋሳ ከተማ ኢኳቶርያል ጊኒያዊ ተከላካይ እና ቶጓዊ አጥቂ በዚህ ሳምንት እንደሚያፈርም ይጠበቃል፡፡

ቶጓዊው አጥቂ ጃኮ አራፋት እና የኢኳቶርያል ጊኒ ዜግነት ያለው ኢምቤሌ ማንጉዌ ከሳምንት በፊት ወደ ኢትዮጵያ በመምጣት በክለቡ የሙከራ ጊዜ ያሳለፉ ሲሆን ተስፋ ሰጪ እንቅስቃሴ ማሳየታቸውን ተከትሎ ክለቡ ሊያስፈርማው ከውሳኔ ደርሷል፡፡ በዛሬው እለት የህክምና ምርመራ ያደረጉ ሲሆን በመጪዎቹ ቀናት ይፈርማሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡ የውጭ ዜጋ ተጫዋቾች የዝውውር መስኮት ከሳምንታት በፊት የተዘጋ ቢሆንም ሀዋሳ ከተማ የሁለቱን ስም ቀደም ብሎ በማስገባቱ ማስፈረም እንደሚችልም ታውቋል፡፡

የ27 አመቱ ጃኮ አራፋት በበርካታ ክለቦች የእግርኳስ ህይወቱን የመራ ሲሆን የራሺየው አንዚ ማካችካላ ፣ የቱርኩ ጋዚየንታስፑር እና የእስራኤሉ አፖኤል ሃክሬ ከተጫወተወተባቸው ክለቦች መካከል የሚጠቀሱ ናቸው፡፡ ጃኮ የህክምና ምርማራውን አጠናቆ የሚፈርም ከሆነ ከፍተኛ የአጥቂ ክፍተት የላለበት ሀዋሳ ከተማ መልካም ዝውውር ይሆናል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

854002_heroa

የኢኳቶርያል ጊኒው ኢንተርናሽናል ኢምቤሌ ማንጉዌ ሌላው ለሀዋሳ እንደሚፈርም የሚጠበቅ ተጫዋች ነው፡፡ ኢምቤሌ በ2013 ስፔን ኢኳቶርያል ጊኒን 2-1 ባሸነፈችበት የወዳጅነት ጨዋታ ባሳየው ድንቅ አቋም የወደፊቱ ኮከብ እንደሚሆን ተስፋ ተጥሎበት ነበር፡፡ ወደ ስኮትላንዱ ሂበርኒያን ክለብ ከተዛወረ በኋላ ግን የእግርኳስ ህይወቱ በፍጥነት ቁልቁል ወርዶ ወደ ቬትናም ለማምራት ተገዷል፡፡

 

Leave a Reply