ፍሬው ኃይለገብርኤል የሲዳማ ቡና ሴቶች ቡድን አሰልጣኝ ሆነ

የኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪሚየር ሊግ የ2008 የውድድር ዘመን ኮከብ አሰልጣኝ ሆኖ የተመረጠው ፍሬው ኃይለገብርኤል የሲዳማ ቡና ሴቶች ቡድን አሰልጣኝ ሆኖ ተሹሟል፡፡

ከደደቢት ጋር የፕሪሚየር ሊግ ቻምፒዮን በሆነ ማግስት በኮንትራት ማደስ ዙርያ ከክለቡ ጋር ባለመስማማቱ የተለያየው ፍሬው ሲዳማ ቡናን በ2 አመት ኮንትራት የተረከበ ሲሆን በአዳዲስ ተጫዋቾች ቡድኑን እንደአዲስ ያዋቀረው ክለብ ውጤታማ የማድረግ ፈተናን ይጋፈጣል፡፡

ሲዳማ ቡና ከአሰልጣኝ በኃይሏ ዘለቀ ጋር የተለያየ ሲሆን ተራማጅ ተስፋዬ እና የካቲት ንጉሴን ጨምሮ ወሳኝ ተጫዋቾችን ለሌሎች ክለቦች አሳልፎ በመስጠት ከዞን ውድድሮች የተመለመሉ ተጫዋቾችን አሰባስቧል፡፡

የኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪሚየር ሊግ አዲሱ የውድድር ዘመን ህዳር 10 ሲጀመር በምድብ ለ የሚገኘው ሲዳማ ቡና የመጀመርያ ጨዋታውን በሲዳማ ደርቢ ከሀዋሳ ከተማ ጋር ሀዋሳ ላይ ያደርጋል፡፡

Leave a Reply