በከፍተኛ ሊግ ክለቦች መካከል የሚካሄደው የደቡብ ካስቴል ዋንጫ ዛሬ ተጀመረ

7 የከፍተኛ ሊግ እና 1 የብሄራዊ ሊግ ክለብ የሚያሳትፈው የደቡብ ካስቴል ዋንጫ የቅድመ ውድድር ዝግጅት ጨዋታ ዛሬ በሀዋሳ ተጀምሯል፡፡

ከህዳር 2 – 11 ድረስ በሀዋሳ የሚካሄደውን ውድድር ቢጂአይ ኢትዮጵያ በካስቴል ቢራ አማካኝነት ስፖንሰር ያደረገው ሲሆን ከአንድ ተጋባዥ ቡድን በስተቀር የደቡብ ክልል ክለቦች ይሳተፉበታል፡፡

የምድብ ድልድሉ ይህን ይመስላል፡-

ምድብ ሀ

ሀዲያ ሆሳዕና ፣ ስልጤ ወራቤ ፣ ጂንካ ከተማ ፣ አምበሪቾ

ምድብ ለ

ደቡብ ፖሊስ ፣ ቡራዩ ከተማ ፣ ወልቂጤ ከተማ ፣ ሀላባ ከተማ

ውድድሩ ዛሬ በይፋ ሲከፈት በምድብ ለ የሚገኙት ቡራዩ ከተማ እና ወልቂጤ ጨዋታቸውን 08:00 ላይ አድርገው ወልቂጤ 1-0 አሸንፏል፡፡ 10:30 ላይ የጀመረው የደቡብ ፖሊስ እና ሀላባ ከተማ ጨዋታ አሁን በመደረግ ላይ ይገኛል፡፡ ውድድሩ ነገ ሲቀጥል በምድብ ሀ 08:00 ሀዲያ ሆሳዕና ከ ጂንካ ከተማ ፤ 10:00 ላይ ስልጤ ወራቤ ከ አምበሪቾ ይጫወታሉ፡፡

የከፍተኛ ሊጉ ህዳር 18 የሚጀመር ሲሆን በውድድሩ ላይ ለሚካፈሉት የደቡብ ክለቦች ጥሩ መዘጋጃ ይሆናቸዋል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

Leave a Reply