የኦሮምያ ዋንጫ ጨዋታዎች እየተካሄዱ ነው

የኦሮምያ ዋንጫ የዘንድሮው ውድድር በሁለት ከተሞች (ባቱ እና ሰበታ) አስተናጋጅነት እየተካሄደ ይገኛል፡፡ በውድድሩ የከፍተኛ ሊግ እና የብሄራዊ ሊግ ክለቦች መካከል እየተካሄደ ሲሆን በሁለቱ ከተሞች የሚካሄዱት ውድድሮች ይህንን ይመስላሉ፡፡

በባቱ አስተናጋጅነት የሚካሄደው ውድድር

ባቱ ከተማ ፣ አርሲ ነገሌ ፣ ለገጣፎ ለገዳዲ ፣ ሞጆ ከተማ ፣ ቡልቡላ

በባቱ ከተማ የሚካሄዱት የዚህ ምድብ ጨዋታዎች ጥቅምት 30 የተጀመሩ ሲሆን በመክፈቻው ባቱ ከተማ ከ ለገጣፎ ለገዳዲ ያለ ግብ አቻ ተለያይተዋል፡፡ ውድድሩ ዛሬም ሲቀጥል ቡልቡላ ሞጆ ከተማን 1-0 አሸንፏል፡፡ አርሲ ነገሌ ከ ለገጣፎ ያረጉት ጨዋ ደግሞ ያለ ግብ አቻ ተለያይተዋል፡፡ የምድብ ሀ ጨዋታዎች እሁድ ሲቀጥሉ ለገጣፎ ለገዳዲ ከ ቡልቡላ 07፡00 ፣ አርሲ ነገሌ ከ ባቱ ከተማ 10፡00 ላይ ይጫወታሉ፡፡

በሰበታ አስተናጋጅነት የሚካሄደው ውድድር

ሰበታ ከተማ ፣ ሱሉልታ ከተማ ፣ ጅማ ከተማ ፣ ነቀምት ከተማ ፣ ለገጣፎ 01

በሰበታ ከተማ የሚካሄደው የዚህ ምድብ ጨዋታ ትላንት የተጀመረ ሲሆን በመክፈቻው ሱሉልታ ከተማ ለገጣፎን 3-0 አሸንፏል፡፡ ሰበታ ከተማ ከ ጅማ ከተማ ደግሞ 0-0 ተለያይተዋል፡፡ ውድድሩ እሁድ ሲቀጥል 08፡00 ላይ ነቀምት ከተማ ከ ለገጣፎ ፣ 10፡00 ላይ ሰበታ ከተማ ከ ሱሉልታ ከተማ ይጫወታሉ፡፡

የውድድሩ ሒደት ከሌሎች ውድድሮች በተለየ መልኩ የጥሎ ማለፍ ሒደት የማይኖረው ሲሆን ከየምድቡ በነጥብ ከፍተኛ የሆኑ ክለቦች የዋንጫ ባለቤት ይሆናሉ፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *