ዋሊድ አታ እና ኦስተርሰንድስ ተለያይተዋል

ኢትዮጵያዊው ኢንተርናሽናል ዋሊድ አታ ከቱርክ መልስ በ2016 የተቀላቀለውን የስዊድኑን ኦስተርሰንድስን መልቀቁን ለሶከር ኢትዮጵያ በሰጠው አስተያየት ተናግሯል፡፡ የመሃል ተከላካዩ ዋሊድ በኦስተርሰንድስ የተሳካ ግዜ ያሳለፈ ሲሆን በውድድር ዓመቱ ሁለት ግቦችን ከመረብ ማሳረፍ ችሏል፡፡

 

ዋሊድ ለመጨረሻ ግዜ ለኦሰተርሰንድስ የተሰለፈው መስከረም 10 ከፋልከንበርግ ጋር በተደረገው ጨዋታ ሲሆን በአምስት ጨዋታዎች ላይ ሳይሰለፍ ቀርቷል፡፡ ዋሊድ በአምስቱ ጨዋታዎች ላይ ያልተሰለፈበት ምክንያት ውሉ በማለቁ መሆኑን አስረድቷል፡፡ ዋሊድ በ2016 የስዊድን ኦልሰቨንስካን ሊግ 1452 ደቂቃዎች ተሰልፎ መጫወት ችሏል፡፡ በቱርኩ ገልሰንበርሊጊ ያልተሳካ የስድስት ወራት ቆይታ በኃላ ነበር ወደ ስዊድን የተመለሰው፡፡ ዋሊድ በነሃሴ ወር ኢትዮጵያ ከሲሸልስ ጋር በአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ዳግም ወደ ዋልያዎቹ ስብስብ ቢመለስም በህመም ምክንያት ሳይጫወት ቀርቷል፡፡

524976358

ኦስተርሰንድስ ሊጉን ስምንተኛነት የጨረሰ ሲሆን ማልሞ በ66 ነጥብ ቻምፒዮን ሆኗል፡፡ ዋሊድ በጥር 2017 በአዲስ ክለብ ለመፈረም ወይም ዳግም ወደ ኦስተርሰንድስ ተመልሶ ውል ስለማደስ ዙሪያ ያለውን ነገር የለም፡፡

Leave a Reply