ተጠናቀቀቅዱስ ጊዮርጊስ3-0አርባምንጭ ከተማ
1′ አቡበከር ሳኒ , 40′ ሳላዲን ሰኢድ , 88′ አዳነ ግርማ
ጨዋታው በቅዱስ ጊዮርጊስ 3-0 አሸነፊነት ተጠናቋል፡፡ ቻምፒዮኖቹ የውድድር ዘመኑን በድል መክፈት ችለዋል፡፡
ተጨማሪ ደቂቃ
መደበኛው የጨዋታ ክፍለ ጊዜ ተጠናቆ 3 ደቂቃ ተጨምሯል፡፡
90′ አስጨናቂ ጸጋዬ የማስጠንቂያ ካርድ ተመልክቷል፡፡
88′ ራምኬል ሎክ ከቀኝ መስመር በግሩም ሁኔታ ያሻገረውን ኳስ አዳነ ግርማ በግንባሩ በመግጨት ከመረብ አሳርፏል፡፡ 3-0
87′ ፈረሰኞቹ ውጤታቸውን አስጠብቀው ለመውጣት ጨዋታውን አቀዝቅዘው እየተጫወቱ ይገኛሉ::
84′ ሳላዲን ሰኢድ ወጥቶ አንዳርጋቸው ይላቅ ገብቷል፡፡
80′ ለ1 አመት ያህል በጉዳት ከሜዳ ርቆ የቆየው ሳላዲን በርጊቾ ተቀይሮ ለመግባት እያሟሟቀ ይገኛል፡፡ ደጋፊዎችም ሞቅ ያለ አቀባበል እያደረጉለት ይገኛሉ፡፡
77‘ አብዱልከሪም ወጥቶ አዳነ ግርማ ገብቷል፡፡
75′ አቡበከር ሳኒ ወጥቶ ራምኬል ሎክ ገብቷል፡፡
71‘ ፍሬዘር ካሳ በሰራው ጥፋት የማስጠንቀቂያ ካርድ ተመልክቷል፡፡
70′ እንዳለ ከበደ ወጥቶ ገብረሚካኤል ያዕቆብ ገብቷል፡፡
63′ በግምት ከ25 ሜትር የተሰጠውን ቅጠት ምት ሳላዲን ሰኢድ ሳጠቀምበት ቀርቷል፡፡
55′ በሁለቱም በኩል በመሃል ሜዳ የተገደበ እንቅስቃሴ እየተደረገ ይገኛል::
ተጀመረ!
ሁለተኛው አጋማሽ የጨዋታ ክፍለጊዜ ተጀመረ::
የመጀመርያው አጋማሽ በቅዱስ ጊዮርጊስ 2-0 መሪነት ተገባዷል
45′ የመጀመርያው አጋማሽ መደበኛ ክፍለጊዜ ተጠናቆ 1 ደቂቃ ተጨምሯል፡፡
40! ሳላዲን ሰኢድ በጥሩ ቅብብል ከ19 ሜትር አካባቢ በመምታት በግሩም ሁኔታ የቅዱስ ጊዮርጊስን መሪነት ወደ ሁለት ከፍ አድርጓል፡፡
33′ ምንያህል ተሸመ ከርቀት አክርሮ የመታውን ኳስ ግብ ጠባቂው አንተነህ እንደምንም አውጥቶታል፡፡
31′ ሳላዲን ሰኢድ የግል ብቃቱን ተጠቅሞ የአርባምንጭ ተከላካዮችን በማተራመስበግራ እግሩ አክርሮ የመታው ኳስ የግቡንአግዳሚ ለትሞ ተመልሷል፡፡ ግሩም ሙከራ
27′ ወርቅይታደል አበበ የውድድር ዘመኑን የመጀመርያ የማስጠንቀቂያ ካርድ ተመልክቷል፡፡
20′ አርባምንጭ ወደ ጨዋታው ለመመለስ ወደ ቅዱ ጊዮርጊስ የግብ ክልል በመጠጋት ተደጋጋሚ ጫና በመፍጠር ላይ ይገኛል፡፡
15′ በሁለቱም በኩል ተመጣጣኝ እንቅስቃሴ ቢታይም ወደ ግብ በፍጥነት በመድረስ ቅዱስ ጊዮርጊስ የተሸለ ነው፡፡
5′ ወንድሜነህ ዘሪሁን በግምት ከ20 ሜተር ርቀት አክርሮ የመታው ኳስ ለጥቂት ወደ ውጪ ወጥቷል፡፡
የውድድር ዘመኑ የመጀመርያ ግብ በፈጣን ሁኔታ በ37ኛው ሴኮንድ ተቆጠረ፡፡ አቡበከር ሳኒ የተከላካዮችን ስህተት ተጠቅሞ ፈረሰኞቹን ቀዳሚ አድርጓል፡፡
ጨዋታው በባለሜዳው ቅዱስ ጊዮርጊስ አማካኝነት ተጀመረ::
የቅዱስ ጊዮርጊስ አሰላለፍ (4-3-3)
22 ዘሪሁን ታደለ
15 ፍሬዘር ካሳ – 12 ደጉ ደበበ (አምበል) – 23 ምንተስኖት አዳነ – 20 ዘካርያስ ቱጂ
27 አብዱልከሪም – 26 ናትናኤል ዘለቀ – 9 ምንያህል ተሾመ
16 በሃይሉ አሰፋ – 7 ሳላዲን ሰኢድ – 18 አቡበከር ሳኒ
ተጠባባቂዎች
1 ፍሬው ጌታሁን ፣ 6 አሉላ ግርማ ፣ 3 መሃሪ መና ፣ 10 ራምኬል ሎክ ፣ 19 አዳነ ግርማ ፣ 25 አንዳርጋቸው ይላቅ ፣ 13 ሳላዲን በርጊቾ
የአርባምንጭ ከተማ አሰላለፍ (4-5-1)
1 አንተነህ መሳ
14 ወርቅይታደል አበበ – 16 በረከት ቦጋለ – 15 ተመስገን ካስትሮ – 22 ፀጋዬ አበራ
7 እንዳለ ከበደ – 4 ምንተስኖት አበራ – 8 አማኑኤል ጎበና (አምበል) – 10 ወንድሜነህ ዘሪሁን – 17 ታደለ መንገሻ
12 አመለ ሚልኪያስ
ተጠባባቂዎች
77 ጃክሰን ፊጣ ፣ 3 ታገል አበበ ፣ 2 ተካልኝ ደጀኔ ፣ 19 ገብረሚካኤል ያዕቆብ ፣ 6 ታሪኩ ጎጀሌ ፣
18 አስጨናቂ ፀጋዬ ፣ 25 አለልኝ አዘነ
ጨዋታው ሊጀምር 15 ደቂቃዎች ቀርቶታል፡፡ የሁለቱም ቡድን ተጫዋቾች ሜዳ ገብተው ሰውነታቸውን በማፍታታት ላይ ይገኛሉ፡፡
ሰላም ክቡራን የድረገጻችን ተከታታዮች! የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የ2009 የውድድር ዘመን በዛሬው እለት ቅዱስ ጊዮርጊስ ከ አርባምንጭ ከተማ በሚያደርጉት ጨዋታ ይጀመራል፡፡ ከዚህ ሰአት ጀምሮ ጨዋታውን የተመለከቱ መረጃዎች በዚሁ ገጽ ላይ እናቀርብላችኋለን፡፡
መልካም ቆይታ!