ዋልያዎቹ ምንም ግብ ሳያስቆጥሩ ከቻን ተሰናበቱ

በአፍሪካ ሃገራት ሻምፒዮን ሺፕ (ቻን) የመጨረሻ ጨዋታዋን ያደረገችው ኢትዮጵያ በጋና አቻዋ 1-0 ተሸንፋ ቀድማ መውደቋን ያረጋገጠችበትን ምድብ ተሰናብታለች፡፡ ዋልያዎቹ በውድድሩ ከያዙት የተጫዋቾች ስብስብ እና ወቅታዊ መነሳሳት አንፃር በቻን ልዩ ትኩረት ከተሰጣቸው ቡድኖች አንዷ ሁና ብትጓዝም ከደካማ እንቅስቃሴ ጋር ምንም ግቦች ሳታስቆጥር እንዲሁም ተስፋ ያለው ነገር ሳታሳይ በጊዜ ተሰናብታለች፡፡

በጋናው ጨዋታ አሰልጣኝ ሰውነት ቢሻው ከቀደመው አሰላለፍ ምንተስኖት አዳነን በቅጣት ባልተሰለፈው አስራት መገርሳ ምትክ ሲያሰልፉ በስብስቡ እጅግ ሲጠበቅ የነበረው የደደቢቱ አማካይ ታደለ መንገሻ የመጨረሻ 5 ደቂቃዎችን ተቀይሮ በመግባት የመጀመርያ የብሄራዊ ቡድን ጨዋታውን አድርጓል፡፡

የብሄራዊ ቡድኑ የቻን ውድቀት በብሄራዊ እግር ኳሱ ለዘመናት የተንሰራፋውንና ባለፉት 2 አመታት የተመዘገበው ውጤት የሸፈነውን ችግር አጉልቶ ያሳየና ትልቅ የቤት ስራ ሰጥቶ ያለፈ ውድድር ሆኗል፡፡

{jcomments on}

ያጋሩ