ጅማ አባ ቡና ከ ኢትዮ ኤሌክትሪክ – ቀጥታ የፅሁፍ ስርጭት

ተጠናቀቀጅማ አባ ቡና0-0ኢትዮ ኤሌክትሪክ


ተጠናቀቀ

ጨዋታው ያለ ግብ በአቻ ውጤት ተጠናቋል፡፡ ጅማ አባ ቡናም በመጀመርያ የፕሪሚየር ሊግ ጨዋታው በታሪክ የመጀመርያ ነጥቡን አስመዝግቧል፡፡

ተጨማሪ ደቂቃ

4ኛ ዳኛው 3 ተጨማሪ ደቂቃዎች አሳይተዋል

86 ኤሌክትሪኮች ከማዕዘን በተሸገረ ኳስ አማካኝነት መልካም የግብ ማስቆጠር አጋጣሚ ቢያገኙም የአባ ቡና ተጫዋቾች ተረባርበው አውጥ

የተጫዋች ለውጥ – ጅማ አባ ቡና

81 ቢንያም ኃይሌ ወጥቶ ቴዎድሮስ ገብረጻድቅ ገብቷል፡፡

77 ዳዊት እስጢፋኖስ ከርቀት አክርሮ የመታው ኳስ በግቡ አናት ወደ ውጪ ወጥቷል፡፡

የተጫዋች ለውጥ – ጅማ አባ ቡና

75 መሃመድ ናስር ወጥቶ ቴዎድሮስ ታደሰ ገብቷል፡፡

የተጫዋች ለውጥ – ኢትዮ ኤሌክትሪክ

72 ሲሴይ ሀሰን ወጥቶ በሃይሉ ተሸገር ገብቷል

70′ በስታድየሙ የተገኘውን ተመልካች በፍፁም የማይመጥን የተቀዛቀዘ እንቅስቃሴ እየተመለከትን እንገናለን፡፡

የተጫዋች ለውጥ – ኢትዮ ኤሌክትሪክ

62 ብሩክ አየለ ወትቶ ዋለልኝ ገብሬ ገብቷል፡፡

ተጀመረ!!!!

ሁለተኛው አጋማሽ የጨዋታ ክፍለ ጊዜ ተጀመረ፡፡


የእረፍት ሰአት ለውጥ

ኪዳኔ አሰፋ ወጥቶ በድሉ መርእድ ገብቷል፡፡


 

እረፍት!!!

የመጀመርያው አጋማሽ ያለግብ ተጠናቋል፡፡

45 የመጀመርያው አጋማሽ መደበኛ ክፍለ ጊዜ ተጠናቆ 1 ደቂ ተጨምሯል፡፡

ቢጫ ካርድ

39 ዳዊት እስጢፋኖስ ቢንያም ሃይሌ ላይ በሰራው ጥፋት የማስጠንቀቂያ ካርድ ተመልክቷል፡፡

37 በጨዋታው ኃይል የተቀላቀለበት እቅስቃሴ እየተካሄደ ይገኛል፡፡ የዳኛው ፊሽካም በተደጋጋሚ እየተሰማ ነው፡፡

ቢጫ ካርድ

27′ ተስፋዬ መላኩ የጨዋታውን የመጀመርያ የማስጠንቀቂያ ካርድ ተመልክቷል፡፡

22′ ጨዋታው ተሟሙቆ ቀጥሏል፡፡ አሜ መሃመድ በመልሶ ማጥቃት ያገኘውን ጥሩ የግብ ማስቆጠር እድል ሳይጠቀምበት ቀርቷል

19′ ፍፁም ገብረማርያም የጨዋታውን የመጀመርያ ለግብ ቀረበ ሙከራ አድርጎ ጀማል ጣሰው አድኖበታል፡፡

17′ ጅማ አባ ቡና ወደ ፕሪሚየር ሊግ ማደግ በጅማ ከተማ እና አካባቢው የሚገኘው የስፖርት አፍቃሪን ምን ያህል እንዳስደሰተ በስታድየሙ የሚታየው ድባብን ማየት በቂ ነው፡፡

11′ ተስፋዬ እና አሜ በሚያደርጉት የሃል አጨዋወት ምክንያት ዳኛው ጨዋታውን አስቁመው ሁለቱን ተጫዋቾች በመገሰጽ ጨዋታው ቀጥሏል፡፡

10′ በሁለቱም በኩል ለግብ የቀረበ ሙከራ ባይደረግም ፈጣን እንቅስቃሴ እየተመለከትን እንገኛለን፡፡

ተጀመረ!!!

ጨዋታው በጅማ አባ ቡና አማካኝነት ተጀምሯል፡፡


09:05 የጅማ አባ ቡና ስፖር ክለብ አመራሮች ለኤሌክትሪክ አባላት የእንኳን ደህና መጣችሁ አቀባበል እያደረጉ ይገኛሉ፡፡ የጅማ መገለጫ የሆነውን ቡና እና የአበባ ስጦታ አበርክተዋል፡፡

09፡03 ሁለቱም ቡድኖች ወደ ሜዳ በመግባት ሰላምታ እየተለዋወጡ ይገኛሉ፡፡

09:55 ጅማ አባ ቡና በታሪኩ ለመጀመርያ ጊዜ የሚያደርገውን የፕሪሚር ሊግ ጨዋታ ለመታደም የተገኙ የክለቡ ደጋፊዎች የጅማ ስታድየምን ከአፍ እስከ ገደፉ ሞልተውታል፡፡ እጅግ አስደማሚ ድባብ እተመለከትን እንገኛለን፡፡


የጅማ አባ ቡና አሰላለፍ (4-4-2)

32 ጀማል ጣሰው

6 ታደለ ምህረቴ – 5 ጀማል ያዕቆብ – 12 ቢያድግልኝ ኤልያስ – 21 በሃይሉ በለጠ

16 ኪዳኔ ተስፋዬ – 17 ቢንያም ኃይሌ – 27 ክሪስቶፈር ንታምቢ – 11 ዳዊት አሰፋ

25 መሃመድ ናስር – 9 አሜ መሃመድ

ተጠባባቂዎች

1 በሽር ደሊል ፣ 18 ኃይለየሱስ ብርሃኑ ፣ 19 ልደቱ ጌታቸው ፣ 15 ቴዎድሮስ ገብረፃዲቅ ፣ 7 በድሉ መርድ ፣ 8 ሱራፌል አወል ፣ 10 ቴዎድሮስ ታደሰ


የኢትዮ ኤሌክትሪክ አሰላለፍ (3-5-2)

22 አቡ ሱሌይማን

21 በረከት ተሰማ – 26 ሲሴይ ሃሰን – 15 ተስፋዬ መላኩ

5 አዲስ ነጋሽ – 19 ደረጄ ሃይሉ – 23 አሸናፊ ሽብሩ – 10 ዳዊት እስጢፋኖስ – 9 ብሩክ አየለ

16 ፍጹም ገብረማርያም – 4 ኢብራሂም ፎፋኖ

ተጠባባቂዎች

1 ኦኛ ኦሞኛ ፣ 24 ዋለልኝ ገብሬ ፣ 8 በሃይሉ ተሻገር ፣ 17 አብዱልሃኪም ሱልጣን ፣ 11 ስንታየሁ ሰለሞን


 

ሰላም ክቡራን የድረገጻችን ተከታታዮች! ትላንት የጀመረው የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 2009 የውድድር ዘመን በዛሬው እለት ቀጥሎ ይውላል፡፡ ጅማ አባ ቡና ከ ኢትዮ ኤሌክትሪክ የሚያደርጉት ጨዋታም ዛሬ ከሚካሄዱ 7 ጨዋታዎች አንዱ ነው፡፡ ከዚህ ሰአት ጀምሮ ጨዋታውን የተመለከቱ መረጃዎች በዚሁ ገጽ ላይ እናቀርብላችኋለን፡፡

መልካም ቆይታ!

 

 

1 Comment

  1. Thanks Dani. For your followers all over the world, please give us more detais like, Head coach and assistant coach of teams, last year performance of the teams, any change in the team from last year, ….

Leave a Reply