ተጠናቀቀኢትዮጵያ ቡና0-3ደደቢት
21′ 52′ 78′ ጌታነህ ከበደ
ተጠናቀቀ
ጨዋታው በደደቢት 3-0 አሸናፊነት ተጠናቋል፡፡ የ2003 እና 2005 የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ከፍተኛ ግብ አስቆጣሪ ጌታነህ ከበደ ከ3 የውድድር ዘመናት በኋላ ለመጀመርያ ጊዜ በተሰለፈበት ጨዋታ ሐት-ትሪክ ሰርቷል፡፡
ተጨማሪ ደቂቃ
4ኛ ዳኛው 3 ተጨማሪ ደቂቃዎች አሳይቷል፡፡
85′ በተለምዶ ዳፍ ትራክ በሚባለው አካባቢ መጠነኛ የደጋፊዎች ግጭት ቢፈጠርም ፖሊስ በቶሎ ተቆጣጥሮታል፡፡
82′ በጨዋታው ተስፋ የቆረጡ ጥቂት የማይባሉ የቡና ደጋፊዎች ሜዳውን ለቀው እየወጡ ይገኛሉ፡፡
ጎልልል!!!! ደደቢት
78′ ጌታነህ ከበደ ከሽመክት ጉግሳ የተሻገረለትን ኳስ በግሩም ሁኔታ አስቆጥሮ ሐት-ትሪክ በመስራት የደደቢትን መሪነት ወደ 3 ከፍ አድርጓል፡፡ ግብ ጠባቂው ክሌመንት በዳንስ ደስታውን እየገለፀ ይገኛል፡፡
የተጫዋች ለውጥ – ደደቢት
75′ ሳምሶን ጥላሁን ወጥቶ አቤል ያለው ገብቷል፡፡
71′ ሳሙኤል ሳኑሚ ከጋቶች የተሸማለትን ኳስ ተንሸራቶ ወደ ግብ ሞክሮ ወደ ውጪ ወጥቶበታል፡፡
የተጫዋች ለውጥ – ኢትዮጵያ ቡና
70′ አማኑኤል ዮሃንስ ወጥቶ ዊልያም ያቡን ገብቷል፡፡
ቢጫ ካርድ
67′ ጌታነህ ከበደ የዳኛውን ውሳኔ በመቃወም ባሳየው ያልተገባ ባህርይ የማስጠንቂያ ካርድ ተመልክቷል፡፡ ደደቢቶች በዛረው ጨዋታ በርካታ የማስጠንቀቂያ ካርዶችን እየተመለከቱ ይገኛሉ፡፡
ቢጫ ካርድ
64′ ስዩም ተስፋዬ ኤልያስ ማሞ ላይ በሰራው ጥፋት የማስጠንቀቂያ ካርድ ተመልክቷል፡፡ በጨዋታው እስካሁን 3 የደደቢት ተጫዋቾ በኤልያስ ማሞ ምክንያት የቢጫ ካርድ ሰለባ ሆነዋል፡፡
62′ በተመሳሳይ መሃመድ ከቀኝ መስመር አፈትልኮ በመግባት የሞከረው ኳስ መረቡን ታኮ ወደ ውጪ ወጥቷል
61′ አብዱልከሪም መሃመድ ከኤልያስ ማሞ የተቀበለውን ኳስ ተጠቅሞ ከደደቢት የግብ ክልል ቀኝ ጠርዝ የመታው ኳስ ኢላማውን ሳጠብቅ ቀርቷል፡፡
ጎልልል!!!! ደደቢት
52′ ጌታነህ ከበደ
ከመስመር የተሻማውን ኳስ ጌታነህ ከበደ ወደ ግብነት በመቀየር የደደቢትን መሪነት ወደ ሁለት አስፍቷል፡፡
52′ አማኑኤል ዮሃንስ አመቻችቶ ያሻገረለትን ኳስ ሳሙኤል ሳኑሚ በቀላሉ ለደደቢቱ ግብ ጠባቂ ክሌመንት አሳቅፎታል፡፡
47′ ኢትዮጵያ ቡናዎች በደደቢት የፍጹም ቅታት ምት ሳጥን ጠርዝ ላይ ያገኙትን የቅጣት ምት ኤልያስ ማሞ መትቶ ክሌመንት በቀላሉ መልሶበታል፡፡
ተጀመረ!!!!
ሁለተኛው አጋማሽ የጨዋታ ክፍለ ጊዜ ተጀምሯል፡፡
እረፍት
የመጀመርያው አጋማሽ የጨዋታ ክፍለ ጊዜ በደደቢት መሪነት ተጠናቋል፡፡
ተጨማሪ ደቂቃ
4ኛ ዳኛው 2 ተጨማሪ ደቂቃዎች አሳይተዋል
45+3′ ጋቶች ፓኖም ከእሱ ጋር በአንድ ሁለት ቅብብል ወደ ውስጥ በመግባት የሞከረው ኳስ በግቡ አናት ወደ ላይ ወጥቷል፡፡
37′ ጌታነህ ከበደ የግብ ጠባቂው ዮሃንስ በዛብህን ከግብ ክልሉ መውጠት ተመልክቶ ከርቀት የሞከረው ኳስ ለጥቂት ወደ ውጪ ወጥቷል፡፡
35′ ኢትዮጵያ ቡናዎች ከሀሪሰን የቀይ ካርድ በኋላ ወደ ጨዋታው ለመመለስ ጥረት በማድረግ ላይ ይገኛሉ፡፡
32‘ አብዱልከሪም መሃመድ ከፍፁም ቅታት ምት ሳጥን ውጪ አክርሮ የመታውን ኳስ ግብ ጠባቂው ክሌመንት በአስደናቂ ሁኔታ አውጥቶታል፡፡
ቢጫ ካርድ
31′ አይቮሪያዊው አማካይ ካድር ኩሊባሊ ሳኑሚ ላይ በሰራው ጥፋት የማስጠንቀቂያ ካርድ ተመልክቷል፡፡
29′ ደደቢቶች በተደጋጋሚ በፈጣን መልሶ ማጥቃት ወደ ቡና የግብ ክልል ለመድረስ ጥረት እደረጉ ይገኛሉ፡፡
ቢጫ ካርድ
28′ ሳምሶን ጥላሁን በኤልያስ ማሞ ላይ በሰራው ጥፋት የማስጠንቀቂያ ካርድ ተመልክቷል፡፡
ጎልልል!!!! ደደቢት
21′ ጌታነህ ከበደ የተገኘውን የቅጣት ምት በግሩም ሁኔታ ወደ ግብነት ቀይሮታል፡፡
የተጫዋች ለውጥ – ኢትዮጵያ ቡና
19′ አስቻለው ግርማ ወጥቶ ግብ ጠባቂው ዮሃንስ በዛብህ ገብቷል
ቀይ ካርድ
14′ ሀሪሰን ሄሱ ከግብ ክልል ውጪ ኳስ በእጅ በመንካቱ በቀይ ካርድ ከሜዳ ተሰናብቷል፡፡
13′ ኢትዮጵያ ቡናዎች ያገኙትን መልካም የግብ ማስቆጠር አጋጣሚ ሳሚ ሳኑሚ ቢያገኝም የግቡ ቋሚ መልሶበታል፡፡
13′ በፈጣን የመልሶ ማጥቃት ደደቢቶች ያገኙትን ኳስ ሰለሞን ሀብቴ ቢሞክርም ሀሪሰን በቀላሉ ይዞበታል፡፡ቢጫ ካርድ
9′ አስራት መገርሳ በኤልያስ ላይ በሰራው ጥፋት የጨዋታውን የመጀመርያ የማስጠንቀቂያ ካርድ ተመልክቷል፡፡ የቅጣት ምቱን ኢኮ ፊቨር ቢሞክረውም በግቡ አናት ወደ ውጪ ወጥቷል፡፡
4′ ኤልያስ ማሞ አክርሮ የመታው ኳስ በግቡ አናት ወደ ውጪ ወጥቷል፡፡
2′ በወንድይፍራው ስህተት የተገኘውን ኳስ ሽመልስ ወደ ጎል አሻምቶ ዳዊት ፍቃዱ ቢሞክረውም ሀሪሰን በቀላሉ ይዞታል፡፡
1′ ጨዋታው በተጀመረ በ35ኛው ሴኮንድ ሳሚ ሳኑሚ የቀድሞው ክቡ አምበል ላይ በሰራው ጥፋት ደደቢቶች ቅታት ምት አግንተዋል፡፡
ተጀመረ
ጨዋታው በኢትዮጵያ ቡና አማካኝነት ተጀምሯል፡፡
09:58 የሁለቱም ቡድን ተጫዋቾች ወደ ሜዳ በመግባት ሰላታ እየተለዋወጡ ይገኛሉ፡፡
የኢትዮጵያ ቡና አሰላለፍ (4-3-3)
ሀሪሰን ሄሱ
አብዱልከሪም መሀመድ – ወንድይፍራው ጌታሁን – ኤኮ ፌቨር – አህመድ ረሽድ
ጋቶች ፓኖም (አምበል) – አማኑኤል ዮሐንስ – ኤልያስ ማሞ
እያሱ ታምሩ – ሳሙኤል ሳኑሚ – አስቻለው ግርማ
ተጠባባቂዎች
ዮሐንስ በዛብህ ፣ መስዑድ መሐመድ ፣ አክሊሉ ዋለልኝ ፣ ሳለአምላክ ተገኝ ፣ ዮሴፍ ዳሙዬ ፣ ሳዲቅ ሴቾ ፣ ያቡን ዊልያም
የደደቢት አሰላለፍ (4-3-3)
ክሌመንት አሼቲ
ስዩም ተስፋዬ – አይናለም ኃይለ – ሰለሞን ሐብቴ – ብርሃኑ ቦጋለ (አምበል)
አስራት መገርሳ – ሳምሶን ጥላሁን – ካድር ኩሊባሊ
ሽመክት ጉግሳ – ጌታነህ ከበደ – ዳዊት ፍቃዱ
ተጠባባቂዎች
ሶፎንያስ ሰይፉ ፣ አቤል ያለው ፣ እያሱ ተስፋዬ ፣ አክሊሉ አየነው ፣ ብርሃኑ አሻሞ ፣ ደስታ ደሙ ፣ ሄኖክ መርሻ
ሰላም ክቡራን የድረገጻችን ተከታታዮች! ትላንት የጀመረው የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የ2009 የውድድር ዘመን በዛሬው እለት ቀጥሎ ይውላል፡፡ በሳምንቱ ታላቅ ጨዋታ ኢትዮጵያ ቡና ከ ደደቢት የሚያደርጉት ጨዋታምዛሬ ከሚካሄዱ 7 ጨዋታዎች አንዱ ነው፡፡ ከዚህ ሰአት ጀምሮ ጨዋታውን የተመለከቱ መረጃዎች በዚሁ ገጽ ላይ እናቀርብላችኋለን፡፡
መልካም ቆይታ!