ሲቲ ካፕ፡ ንግድ ባንክ ወደ ሩብ ፍፃሜ ማለፉን አረጋገጠ

በሲቲ ካፕ የ4ኛ ቀን ውሎ በምድብ 1 የሚገኙት የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እና መከላከያ ድል ቀንቷቸዋል፡፡ በ9፡00 በመጀመርያ ጨዋታው ሽንፈት ያስተናገደው መከላከያ ደደቢትን 2-0 አሸንፎ ወደ ሩብ ፍፃሜ የመግባት እድሉን አለምልሟል፡፡ ፍሬው ሰለሞን እና አዲስ ፈራሚው ሙሉአለም ጥላሁን ለመከላከያ ግቦቹን ሲያስቆጥሩ መከላከያ በአንፃራዊነት ከደደቢት በተሻለ መልኩ ወሳኝ ተጫዋቾችን ማሰለፉ ለድሉ አስተዋፅኦ አበርክቷል፡፡

በ11፡00 ሲጠበቅ የነበረው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እና ኢትዮጵያ ቡና ጨዋታ በተመልካች እምብዛም ሳይታጀብ በንግድ ባንክ 1-0 አሸናፊነት ተጠናቋል፡፡ከትላንት በስቲያ ህይወቱ ያለፈው እውቁ የኢትዮጵያ ቡና ደጋፊ ‹‹ ቼሪ ›› በደጋፊዎች በታሰበበት ጨዋታ ጫላ ድሪባ ለኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የማሸነፍያዋን ግብ አስቆጥሯል፡፡ ንግድ ባንክ ከ2 ጨዋታ ሁለቱንም በድል በማጠናቀቁ ከወዲሁ ወደ ሩብ ፍፃሜ ማለፉን አረጋግጧል፡፡

ምድቡን ንግድ ባንክ በ6 ነጥብ ሲመራ መከላከያ በ3 ኢትዮጵያ ቡና እና ደደቢት በ1 ነጥብ ተከታታዮቹን ደረጃ ይዘዋል፡፡ ውድድሩ ረቡእ የሚቀጥል ሲሆን በምድብ 2 ቅዱስ ጊዮርጊስ ከ መብራት ኃይል ኢትዮጵያ መድን ከ ሙገር ሲሚንቶ ይጫወታሉ፡፡

አጠቃላይ መረጃዎች

ምድብ 1

ኢትዮጵያ ቡና 0-0 ደደቢት

መከላከያ 1-2 ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ

ደደቢት 0-2 መከላከያ

ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ 1-0 ኢትዮጵያ ቡና

1.ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ – 2 – (+2) – 6

2.መከላከያ – 2 – (+1) – 3

3.ኢትዮጵያ ቡና – 2 – (-1) – 1

4.ደደቢት – 2 – (-2) – 1

ምድብ 2

መብራት ኃይል 1-1 ኢትዮጵያ መድን

ቅዱስ ጊዮርጊስ 1-0 ሙገር ሲሚንቶ

1.ቅዱስ ጊዮርጊስ – 1 – (+1) – 3

2.ኢትዮጵያ መድን – 1 – (+0) – 1

3.መብራት ኃይል – 1 – (+0) – 1

4.ሙገር ሲሚንቶ – 1 – (-1) – 0

{jcomments on}

ያጋሩ