ሲቲ ካፕ ፡ ቅዱስ ጊዮርጊስ የመጀመርያ ጨዋታውን በድል ጀመረ

የአአ ከተማ ዋንጫ የምድብ ሁለት የመጀመርያ ጨዋታዎች ከቀትር በኃላ ተካሂደው መብራት ኃይል ነጥብ ሲጥል ቅዱስ ጊዮርጊስ አሸንፏል፡፡ 9 ሰአት በተጀመረው የመብራት ኃይል እና ኢትዮጵያ መድን ጨዋታ በአሰልቺ አንድ ሁለት ቅብብሎች ታጅቦ 1-1 አቻ ውጤት ተጠናቋል፡፡ ለእረፍት ከመውጣታቸው በፊት ግብ በማስቆጠር ቅድሚያውን የያዙት ሰማያዊዎቹ ነበሩ፡፡ በሁለተኛው አጋማሽ የተሻለ ሆነው የቀረቡት መብራት ኃይሎች የአቻነቷን ግብ አስቆጥረው ጨዋታው በዛው ውጤት ተጠናቋል፡፡

በ11 ሰአት ተጋባዡ ሙገር ሲሚንቶን የገጠመው የ3 ጊዜ ሻምፒዮኑ ቅዱስ ጊዮርጊስ በቀድሞው የሙገር አጥቂ ፍፁም ገብረማርያም ብቸኛ ግብ 1-0 አሸንፎ ወጥቷል፡፡ ጨዋታው ተመጣጣን እና በግብ ሙከራዎች የታጀበ ሲሆን በወጣት ተጫዋቾች ለገቡት ቅዱስ ጊዮርጊሶች የተስፋዬ አለባቸው እና ፍፁም ገብረማርያም ወደ ሜዳ መመለስ አስደሳች ሆኖላቸዋል፡፡ እንደ ቅዱስ ጊዮርጊስ ሁሉ በአመዛኙ በዋጣቶች የገቡት ሙገሮችም ግብ ጠባቂው ሳምሶን አሰፋን ፈትነውት አምሽተዋል፡፡

ምድቡን ቅዱስ ጊዮርጊስ በ 3 ነጥብ ሲመራ መድን እና መብራት ኃይል በ1 ነጥብ ይከተላሉ፡፡ የሲቲ ካፕ 4ኛ ቀን ውሎ ማክሰኞም ሲቀጥል በ9፡00 ደደቢት ከ መከላከያ በውድድር አመቱ ለሁለተኛ ጊዜ በድጋሚ ይገናኛሉ፡፡ በ11፡00 የዘንድሮው ጠንካራ ቡድን ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በመጀመርያ ጨዋታ አቻ የወጣው ኢትዮጵያ ቡናን ይገጥማል፡፡

አጠቃላይ መረጃዎች

ምድብ 1

ኢትዮጵያ ቡና 0-0 ደደቢት

መከላከያ 1-2 ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ

1.ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ – 1 – (+1) – 3

2.ደደቢት – 1 – (+0) – 1

3.ኢትዮጵያ ቡና – 1 – (+0) – 1

4.መከላከያ – 1 – (-1) – 0

ምድብ 2

መብራት ኃይል 1-1 ኢትዮጵያ መድን

ቅዱስ ጊዮርጊስ 1-0 ሙገር ሲሚንቶ

1.ቅዱስ ጊዮርጊስ – 1 – (+1) – 3

2.ኢትዮጵያ መድን – 1 – (+0) – 1

3.መብራት ኃይል – 1 – (+0) – 1

4.ሙገር ሲሚንቶ – 1 – (-1) – 0

{jcomments on}

ያጋሩ