የኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ እና ብሄራዊ ሊግ ክለቦች የሚሳተፉባቸው የቅድመ ውድድር ጨዋታዎች በሀዋሳ ፣ ባህርዳር ፣ ባቱ እና ሰበታ ከተሞች እየተካሄዱ ይገኛሉ፡፡
የደቡብ ካስቴል ዋንጫ
የቢጂአይ ኢትዮጵያ ምርት የሆነው ካስቴል ቢራ ስፖንሰር ያደረገው የደቡብ ካስቴል ዋንጫ በሁለት ምድብ ተከፍሎ እየተካሄደ ሲሆን የምድብ ጨዋታዎቹም በዛሬው እለት ፍፃሜያቸውን አግኝተዋል፡፡ በምድቦቹ የተመዘገቡት ውጤቶች እና ወደ ግማሽ ፍጻሜ ያለፉት ክለቦች የሚከተሉት ናቸው፡-
ምድብ ሀ
አርብ ህዳር 2
ወልቂጤ ከተማ 1-0 ቡራዩ ከተማ
ደቡብ ፖሊስ 1-3 ሀላባ ከተማ
እሁድ ህዳር 4
ሀላባ ከተማ 3-1 ቡራዩ ከተማ
ወልቂጤ ከተማ 1-0 ደቡብ ፖሊስ
ማክሰኞ ህዳር 6
ደቡብ ፖሊስ 1-0 ቡራዩ ከተማ
ወልቂጤ ከተማ 3-3 ሃላባ ከተማ
ሰንጠረዥ
1 ሀላባ ከተማ 3 (+4) 7
2 ወልቂጤ ከተማ 3 (+2) 7
————
3 ደቡብ ፖሊስ 3 (-2) 3
4 ቡራዩ ከተማ 3 (-4) 0
ምድብ ለ
ቅዳሜ ህዳር 3
ሀዲያ ሆሳዕና 1-0 ጂንካ ከተማ
ወራቤ ከተማ 0-1 አምባሪቾ
ሰኞ ህዳር 5
ሀዲያ ሆሳእና 0-1 ስልጤ ወራቤ
አምባሪቾ 1-2 ጂንካ ከተማ
ረቡዕ ህዳር 7
ሀዲያ ሆሳዕና 1-1 አምባሪቾ
ስልጤ ወራቤ 1-1 ጂንካ ከተማ
ሰንጠረዥ
1 ጂንካ ከተማ 3 (0) 4
2 አምባሪቾ 3 (0) 4
———-
3 ሀዲያ ሆሳዕና 3 (0) 4
4 ሰልጤ ወራቤ 3 (0) 4
የግማሽ ፍፃሜ ጨዋታዎች
አርብ ህዳር 9
07፡00 ሀላባ ከተማ ከ አንባሪቾ
09፡00 ጂንካ ከተማ ከ ወልቂጤ ከተማ
የኦሮምያ ዋንጫ
በሁለት ከተሞች (ባቱ እና ሰበታ) እየተካሄደ የሚገኘው ውድድር ከተጀመረ ሳምንት አስቆጥሯል፡፡
በባቱ ከተማ እየተካሄደ ባለው ውድድር በ2ኛ ቀን እሁድ እለት በተደረጉ ጨዋታዎች ለገጣፎ ለገዳዲ ቡልቡላን 2-0 ፤ ባቱ ከተማ ደግሞ አርሲ ነገሌን 1-0 ማሸነፍ ችለዋል፡፡
የ3ኛው ቀን ጨዋታዎች ማክሰኞ የተደረጉ ሲሆን አርሲ ነገሌ ሞጆ ከተማን 3-2 ፤ ባቱ ከተማ ቡልቡላን 3-0 አሸንፈዋል፡፡
የዚህ ከተማ ውድድር 4ኛ ቀን ጨዋታዎች ነገ ሲቀጥሉ 07:00 ቡልቡላ ከ አርሲ ነገሌ ፤ ሞጆ ከ 09:00 ለገጣፎ ለገዳዲ ይጫወታሉ፡፡ የውድድሩ የመጨረሻ ጨዋታዎች ደግሞ ቅዳሜ ሲቀጥሉ ከፍተኛ ነጥብ ያስመዘገበው ክለብ የዋንቻ ባለቤት ይሆናል፡፡
ከ3 ጨዋታዎች በኋላ የክለቦች ደረጃ ይህንን ይመስላል፡-
1 ባቱ ከተማ 3 (+3) 7
2 ለገጣፎ ለገዳዲ 2 (+2) 4
3 አርሲ ነገሌ 2 (0) 3
4 ቡልቡላ 3 (-4) 3
5 ሞጆ ከተማ 2 (-2) 0
በሰበታ ከተማ እየተካሄደ በሚገኘው ውድድር 2ኛ ቀን ጨዋታ እሁድ ሰበታ ከተማ ነቀምት ከተማን ፣ ጅማ ከተማ ሱሉልታ ከተማን በተመሳሳይ 1-0 በሆነ ውጤት አሸንፈዋል፡፡ ማክሰኞ በቀጠለው የ3ኛ ቀን ጨዋታዎች ጅማ ከተማ ለገጣፎን 3-1 ፤ ሱሉልታ ከተማ ነቀምት ከተማን 2-0 አሸንፈዋል፡፡
የውድድሩ 4ኛ ቀን ጨዋታዎች ነገ ሲቀጥሉ 08:00 ላይ ሰበታ ከተማ ከ ሱሉልታ ከተማ ፤ 10:00 ላይ ለገጣፎ 01 ከ ነቀምት ከተማ ይጫወታሉ፡፡ እንደ ባቱ ከተማው ውድድር የሰበታውም ቅዳሜ የሚጠናቀቅ ሲሆን ከፍተኛ ነጥብ ያስመዘገበው ክለብ የዋንጫ ባለቤት ይሆናል፡፡
ከ3 ጨዋታዎች በኋላ የክለቦች ደረጃ ይህንን ይመስላል፡-
1 ጅማ ከተማ 3 (3) 7
2 ሱሉልታ ከተማ 3 (4) 6
3 ሰበታ ከተማ 2 (1) 4
4 ነቀምት ከተማ 2 (-3) 0
5 ለገጣፎ 2 (-5) 0
የአማራ ዋንጫ
4 የከፍተኛ እና የብሄራዊ ሊግ ክለቦች የሚሳተፉበት የአማራ ዋንጫ በባህርዳር ዩኒቨርሲቲ ሜዳ እየተደረገ ይገኛል፡፡ ውድድሩ እሁድ ሲጀመር አማራ ውሃ ስራ አማራ ፖሊስን 4-1 ሲያሸንፍ ባህርዳር ከተማ ወሎ ኮምቦልቻን 1-0 ረቷል፡፡ የውድድሩ ሁለተኛ ቀን ጨዋታዎች ትላንት ሲቀጥሉ አማራ ውሃ ስራ ባህርዳር ከተማን 2-1 ፤ ወሎ ኮምቦልቻ አማራ ፖሊስን 2-0 አሸንፈዋል፡፡
ውድድሩ በመጪው እሁድ ሲጠናቀቅ 07፡00 ላይ ባህርዳር ከተማ ከ አማራ ፖሊስ ፤ 09:00 ላይ ወሎ ኮምቦልቻ ከ አማራ ውሃ ስራ ይጫወታሉ፡፡
የደረጃ ሰንጠረዥ
1 አማራ ውሃ ስራ 2 (+4) 6
2 ወሎ ኮምቦልቻ 2 (+1) 3
3 ባህርዳር ከተማ 2 (0) 3
4 አማራ ፖሊስ 2 (-5) 0