በሲቲ ካፕ፡ አብይ በየነ ለንግድ ባንክ 3 ነጥብ አስገኘ

8ኛው የአአ ከተማ ዋንጫ የምድብ አንድ 2ና ጨዋታ ዛሬ ተካሂዶ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ መከላከያን 2-1 አሸንፏል፡፡ በመቶዎች የሚቆጠሩ ተመልካቾች በተከታተሉት ጨዋታ ግብ በማስቆጠር ቅድሚያውን የያዙት ወይን ጠጅ ለባሾቹ በናድር ኢብራሂም አማካኝነት ነው፡፡ መከላከያ ተቀይሮ በገባው ፍሬው ሰለሞን አማካኝነት አቻ ቢሆንም አንድ ደቂቃ ባልሞላ ጊዜ ውስጥ አብይ በየነ ለኢትዮጵያ ንግድ ባንክ 2ኛዋን ግብ አስቆጥሯል፡፡ ከግቧ መቆጠር በኋላ መከላከያዎች ጫና ቢፈጥሩም ግብ ማስቆጠር አልቻሉም፡፡ በተለይም በመጨረሻዎቹ ደቂቃዎች የግቡ ብረት የመለሱባቸው 2 የግብ እድሎች የሚያስቆጩ ነበሩ ፡፡በጨዋታው ኢትዮጵያ ቡናን በአወዛጋቢ ሁኔታ ለቆ መከላከያን የተቀላቀለው ሙሉአለም ጥላሁን ለአዲሱ ክለቡ 70 ደቂቃዎች ያህል ተሰልፏል፡፡

ምድብ አንድን ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በ3 ነጥብ ሲመራ ባለፈው እሁድ አቻ የተለያዩት ኢትዮጵያ ቡና እና ደደቢት በ1 ነጥብ ይከተላሉ፡፡

{jcomments on}

ያጋሩ