ኢትዮጵያ በመክፈቻው ተሸነፈች

በ3ኛው የአፍሪካ ሻምፒዮን ሺፕ (ቻን) የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን በሊበያ 2-0 ተሸነፈች፡፡ በአፍሪካ ዋንጫ እና በአለም ዋንጫ ማጣር ግሩም ጉዞ አድርጋ የነበረችው ኢትዮጵያ ስብስቧን ብዙም ሳትለውጥ በመጓዟ በቻን ጥሩ ውጤት ታስመዘግባለች በሚል ልዩ ትኩረት ተሰጥቷት ነበር፡፡ ነገር ግን ዋልያዎቹ እንደተጠበቀው ሳይሆኑ 2-0 ተሸንፈዋል፡፡

በቀድሞው የአትሌቲክ ቢልባኦ አወዛጋቢ አሰልጣኝ ሃዚየር ክሌሜንቴ የሚሰለጥኑት ሊቢያዎች የአንበሉ ደጉ ደበበን ስህተት ተጠቅመው ግብ ያስቆጠሩት ገና ጨዋታው በተጀመረ በ3ኛው ደቂቃ ነው፡፡ከግቡ መቆጠር በኋላ ዋልያዎቹ የተሸለ እንደሚንቀሳቀሱ ቢጠበቅም ሚዛኑ የተፋለሰ ፣ ግልፅ የጨዋታ እቅድ የሌለው ፣ በቂ የግብ እድል መፍጠር የተሳነው እና ውህደት የማይታይበት ሆኖ ቀርቧል፡፡

ምድቡን ሊቢያ በ3 ነጥብ እና 2 የግብ ልዩነት ስትመራ ኮንጎ ብራዛቪልን 1-0 የረታችው ጋና በተመሳሳይ ነጥብ ትከተላለች፡፡ የምድብ ሶስት ቀጣይ ጨዋታዎች በመጪው አርብ የሚደረጉ ሲሆን በ12 ሰአት ሊቢያ ከ ጋና ኢትዮጵያ ከኮንጎ ብራዛቪል ይጫወታሉ፡፡

{jcomments on}