የውድድር ዘመኑ አጋማሽ የመጨረሻ ሳምንት የፕሪሚየር ሊጉ መርሃ ግብር የአዲስ አበባ ጨዋታዎች የቀደሙት የውድድር ዘመናት ቻምፒኖቹ ቅዱስ ጊዮርጊስ እና ደደቢት እሁድ ባደረጉት ጨዋታ በብራዚላዊው ኔይደር ዶ ሳንቶስ የሚመራው ቅዱስ ጊዮርጊስ የአሰልጣኝ ዮሃንስ ሳህሌውን ደደቢት 2-0 አሸንፎ ወጥቷል፡፡ በጨዋታው ደደቢት ግልፅና በቀላለሉ ሊጣይ የሚችል የ4-2-3-1 የተጫዋቾች የሜዳ ላይ አደራደርን ተግባራዊ ሲያደርጉ ቅዱስ ጊዮርጊስ ደግሞ በተጫዋቾች የቦታ አጠባበቅ (Positioning Discipline) ላይ መጠነኛ ችግር የተስተዋለበትን 4-4-2 ፎርሜሽን ተጠቅመዋል፡፡
ምስል 1
የመጀመርያ አጋማሽ የጨዋታ ሒደት
ፈረሰኞቹ በዚህኛው የጨዋታ ክፍለ ጊዜ በ4-4-2 የሜዳ ላይ አደራደር ከሁለቱ የመል አማካዮች ለአንደኛው (ምንተስኖት አዳነ) የበለጠ ወደ ፊት የመጠጋት ነፃነትን የሰጡ በሚመስል መልኩ ተጫዋቹ የቡድኑ የማጥቃት እንቅስቃሴ ላይ ቀጥተኛ ተሳትፎ እንዲኖረው አድርጓል፡፡
ይህ የአጨዋወት ስልት በተለምዷዊው 4-4-2 ፎርሜሽን የሚተገበረውን የመሃል አማካዮች የሜዳ ውስጥ የጎንዮሽ የቦታ ላይ አያያዝ (Lateral Positioning) የተከተለ ሳይሆን በሜዳው ቁመት በቅርብ ርቀት (በጨዋታው በይበልጥ በተከላካይ አማካይነት ሚና በተሰለፈው) ከተስፋዬ አለባቸው ጋር ፊትና ኋላ በመሆን ነበር ሲጫወቱ የነበረው፡፡ ይህ አቀራረብ የተከላካይ አማካዩ ተስፋዬ ይበልጥ ለኋለኛው የተከላካይ መስመር (Back 4) ጠንካራ ሽፋን እንዲሰጥና ምንተስኖት ደግሞ ከአጥቂዎቹ ጀርባ በተደጋጋሚ በመገኘት የፊት መስመሩንና የመሃል ክፍሉን ለማገናኘት (Link ለማድረግ) አስችሎታል፡፡ ከዚህ በተጨማሪም ምንተስኖት የደደቢቱን ስዩም ተስፋዬ (የተከላካይ አማካይ) ተጭኖ በመጫወት (Press በማድረግ) የተጋጠጣሚያቸው የቀኝ የመስመር አማካይ (ሳሚ ሳኑሚ) ይበልጥ ወደኋላ እንዲያፈገፍግ አድርጎታል፡፡
ቅዱስ ጊዮርጊሶች ጨዋታው በተጀመረበት የመጀመርያዎቹ 15 ደቂቃዎች ውስጥ በተደጋጋሚ የግብ ሙከራዎችን እንዲያደርጉ ካስቻሉዋቸው ምክንያቶች መካከል የደደቢትን ተጫዋቾች መነጣጠል (በተለይም ነሁለቱ በየአማካይ መስመሮቻቸው መካከል – በተከላካይ አማካዮችና በአጥቂ አማካዮች መካከል ሰፊ ክፍተት ነበር፡፡) የተመረኮዘ ነበር፡፡
የሳላዲን የቅጣት ምት ሙከራ እና የአዳነ ግርማ በግንባር የተገጨ ኳስ ሙከራ መሰረቱ ክፍተት ከተገኘባቸው ቦታዎች የተነሱ ነበሩ፡፡ በ16ኛው ደቂቃ ላይም በአምናዎቹ ቻምፒዮኖች ከፍተኛ የማጥቃት ቻና የተገኘችውን የቅታት ምት ኳስ በኃይሉ አሰፋ የመከላከል መስመር ሰርተው ከቆሙት የደደቢት ተጫወቾች ጎን ለሳላዲን የሰጠውን ኳስ ተከላካዩ አክሮባቲክ በሆነ ሁኔታ ግብ ያደረጋት ኳስ ሒደት ማራኪ ነበር፡፡
ሰማያዊዎቹ በጨዋታው በሁሁቱም መስመሮች ሚዛናዊ ያልሆነ የመከላከል እና የማጥቃት እንቅስቃሴ አሳይተዋል፡፡የመስመር አማካዮቹ (ሳኑሚ እና በረከት) ከጀርባቸው ከነበሩት የመስመር ተከkላካዮች (ብሩክ እና ሰለሞን) ርቀው በላይኛው የሜዳ ክፍል መገኘታቸው የጊዮርጊስ ፉልባኮችን (ዘካርያስ እና አንዳርጋቸው) የፊት ለፊት የማጥቃት እንቅስቃሴ (overlapping movement) እንዲገቱ (stifle እንዲያደርጉ) ቢያስችላቸውም የራሳቸው ፉልባኮች በጎንዮሽም በፊት ለፊትም ለመሃል ተከላካዮች ቀርበው መጫወታቸው (Flat back 4) አፊ የመጫወቻ ክፍተት ለተጋጣሚው እንዲተዉ አድርጓቸዋል፡፡ አሉላ ፣ በኃይሉ እና ዳዋ ኢቲሳ በመስመር ተደጋጋሚ ሲያሳዩ የነበሩት የኳስ ቁጥጥር የበላይነት እና ጫና መነሻውም ይሄ ነበር፡፡
ምስል 2
ሁለተኛው አጋማሽ
ሁለቱም ቡድኖች የተጫዋቾች ለውጥ አድርገው የተመለሱበት የጨዋታ ክፍለ ጊዜ ነው፡፡ ደደቢቶች የተጋጣሚ የኳስ አቅጣጫ እና እንቅስቃሴን የተመረኮዘ (Ball oriented Movement) አጨዋወት በተከላካይ መስመራቸው ላይ በተደጋጋሚ ታይቷል፡፡ የሰማያዊዎቹ Back 4 ጊዮርጊሶች የሚያጠቁበትን መስመር የተከተለ ነበር፡፡ ተጋጣሚ ኳስን በተቆጣጠረበት መስመር አጥብበው እና ተጠጋግተው መከላከላቸው ያን መስመር እንዲቆጣጠሩ ቢያስችላቸውም በተቃራኒው ያለው ቦታ ደካማ ክፍል (Weaker Zone) በጊዮርጊስ አማካዮች እና አጥቂዎች ጥቅም ላይ ሲውል ነበር፡፡ በተከላካይ አማካዮች የጎንዮሽ ቦታ ላይ የመቀባበያ አማራጮችን (Passing Lane options) የመፍጠር ኃላፊነት የነበረባቸው እነ ከፊታቸው የነበረውን ሰፊ ክፍተት (space) ማጥበብ የነበረባቸው ሰለሞን እና ብሩክ ወደኋላ በማፈግፈጋቸው በማጥቃት እንቅስቃሴያቸው ላይ ያላቸው ተሳትፎ አናሳ እንዲሆን አድርጎታል፡፡ ይህም የተከላካይ አማካዮቹ (ስዩም እና ሄኖክ) ላይ ሰፊ የጎንዮሽ ክፍተት እንዲሸፍኑ ጫና አብዝቶባቸዋል፡፡በተለይም ከተፈጥሮአዊ የቀኝ ፉልባክ ይልቅ በልለመደው የተከላካይ አማካይ ሚና የተሰለፈው ስዩም ተስፋዬ የሜዳውን ስፋት በአግባቡ ሲጠቀሙበት በዋሉት አሉላ እና በኃይሉ ሲፈተን ነበር፡፡ ቡድኑ ከማጥቃት ወደ መከላከል ሲያደርግ የነበረው ሽግግር (Defending Transition) ላይም በቶሎ የመከላከል ቅርፅን የመያዝ ችግር ተስተውሎበታል፡፡ በብቸኛ አጥቂነት የተሰለፈው ዳዊት ከቡድኑ ተነጥሎ የታየበት ረጅም የጨዋታ ጊዜም በጨዋታው የታየ ትልቁ የደደቢት ችግር ነበር፡፡ ተጫዋቹን ከአማካዮች ጋር ለማገናኘት የሚያስችል ቦታ ላይ የነበረው ሳምሶን ጥላሁን ወደኋላ ለተከላካይ አማካዮች ተጠግቶ መጫወቱ ዳዊትን ይበልጥ ለብቻው እንዲታይ አስችሎታል፡፡
ምስል 3
የበኃይሉ አሰፋ ተፅእኖ
በኃይሉ አሰፋ ለቡድኑ በሚሰለፍባቸው ሁለቱም መስመሮች ላይ ተመጣጣኝ የሆነ ግልጋሎት የሚያበረክት አማካይ ነው፡፡ ተጫዋቹ የጊዮርጊስን የማጥቃት አጨዋወት ከማፍጠኑ በተጨማሪ ቡድኑ በመከላከል ሂደት (defending Phase) ላይ ሲሆን ከተከላካይ አማካዮቹ ጎን በbመገኘት እየሰጠ የሚገኘው ጥቅም የሚያስወድሰው ነው፡፡ ከዚህም ሌላ ተጋጣሚ በመስመር ወይም ከተከላካዮች ጀርባ የሚተውን ክፍተት በመጠቀም እና ሌሎቹ የቡድኑ አጋሮችም ክፍተቱን የሚጠቀሙበት እድሎች በማመቻቸት በኩል ያለው ሚና አብዛኛውን ጊዜ ውጤታማ ሲያደርገው ይታያል፡፡ ለታሰበላቸው የቡድን አጋሮቹ የሚሰጣቸው ኳሶችና የሚያደርጋቸው የግብ ሙከራዎችም የተሳኩ ናቸው፡፡
በ53ኛው ደቂቃ ላይ ስዩም ትቶቶ በሄደው ቦታ ላየይ አሉላ የቡድኑን 2ኛ ግግብ እንዲያስቆጥር አስተዋፅኦው የጎላ ነበር፡፡ ጊዮርጊሶች ጨዋታውን በቀኝ መmስመራቸው ላይ አመዝነው በነበረበት ሰአት የደደቢቶችን ደካማ መስመር (ስየም ወደ ግራው የመሃል ክፍል አድልቶ በነበረበት ሁኔታ) ተጠቅመው አሸናፊነታቸውን የምታጠናክርላቸውን ግብ አግኝተዋል፡፡
በኃይሉ በላይኛው የሜዳ ክፍል የማጥቃት ማዕዘናትን (Attacking Angles) የሚያሰፋበት መንገድ ጊዮርጊሶች በማጥቀቃት እንቅስቃሴያቸው በተጋጣሚ የግብ ክልል ተጭነው መጫወት እንዲችሉ እያደረጋቸው ይገኛል፡፡
ምስል 4