የኢትዮጵያ ዋንጫ ዛሬ ይጀመራል

የ2007ዓ.ም. የኢትዮጵያ ዋንጫ (ጥሎ ማለፍ) ውድድር ዛሬ በሚደረጉ ሁለት ጨዋታዎች ይጀመራል፡፡ 16ቱ የፕሪሚየር ሊጉ ክለቦች ብቻ የሚካፈሉበት የዘንድሮው ውድድር ከወዲሁ በክለቦች ላይ ቅሬታን አስከትሏል፡፡ ጨዋታዎቹ የፕሪሚየር ሊጉ 1ኛ ዙር እረፍት ላይ መደረጋቸው ክለቦቹን አማሯቸዋል፡፡

ዛሬ ሁለቱም ጨዋታዎች በአበበ ቢቂላ ስታድየም የሚደረጉ ሲሆን በ8፡00 አርባምንጭ ከነማ ከ ሙገር ሲሚንቶ ይፋለማሉ፡፡ ሁለቱ ቡድኖች በአንደኛው ዙር የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ አሰላ ላይ ተገናኝተው አርባምንጭ በሙሉአለም መስፍን ግብ 1-0 አሸንፎ መመለሱ ይታወሳል፡፡

ከሙገር እና አርባምንጭ ጨዋታ በመቀጠለ 10፡00 ላይ የሊጉ መሪ ሲዳማ ቡና በሊጉ ግርጌ ላይ ከሚገኘው ወልድያ ጋር ይጫወታል፡፡ ሁለቱ ቡድኖች ዘንድሮ ባደረጉት የሊግ ጨዋታ ይርጋለም ላይ ሲዳማ ቡና 1-0 ማሸነፉ ይታወሳል፡፡

የውድድሩ ቀጣይ ጨዋታዎች የሚከተሉት ናቸው፡-

ሀሙስ ጥር 28 – 08፡00 ዳሽን ቢራ ከ መከላከያ

ሀሙስ ጥር 28 – 10፡00 ደደቢት ከ ሀዋሳ ከነማ

ቅዳሜ ጥር 30 – 08፡00 ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከ ኤሌክትሪክ

ቅዳሜ ጥር 30 – 10፡00 አዳማ ከነማ ከ ደደቢት

 

ያጋሩ