ውበቱ አባተ ከአህሊ ሼንዲ ጋር ተለያዩ

አሰልጣኝ ውበቱ አባተ ከሱዳኑ አህሊ ሼንዲ ጋር የነበራቸው ግንኙነት ማብቃቱን በፌስቡክ ገፃቸው አስታውቀዋል፡፡ አሰልጣኙ ስለ መለያየታቸው በፌስቡክ ገፃቸው ያሰፈሩት ፅሁፍ ይህንን ይመስላል፡፡

 

”ላለፉት 1 አመት ከ6 ወር በሱዳን ቆይታዩ እጅግ አስደሳች ጊዜያትን አሳልፌያለሁ:: አህሊ ሸንዲን በቅድሚያ በምክትልነት ባገለግልም በቆይታ የተሰጠኝን የዋና ሃላፊነት ሚና በተገቢው በመወጣት ክለቡ በ3ኝነት እንዲያጠናቅቅ በማሰቻል የኮንፌዴሬሽን ተሳታፊ እንዲሆን የበኩሌን አሰተዋጾ አበርክቻለሁ::
ይሁን እንጂ ከክለቡ ጋር የነበረን የውል ጊዜ መጠናቀቁን ተከትሎ አስቀድሜ በአዲስ ኮንትራት ዙሪያ ብንነጋገርም አዲስ ኮንትራት የመፈራረሙ ሂደት ከእልባት ላይ መድረስ አልቻለም:: ከውልና ኮንትራት ውጪ ለተጨማሪ ወር ቡድኑንን እያገለገልኩ ቢሆንም ይህ አካሄድ ጤናማ ካለመሆኑ በተጨማሪ የሙያው ስእብናም የማይፈቅድ በመሆኑ ከሂላል ጨዋታ ማግስት ጀምሮ ቡድኑን በመሰናበት ሁኔታው እልባት እሰከሚያገኝ ላለማሰልጠን በመወሰን የሽንዲ ቆይታየ መጠናቀቁን እየገለጽኩ ለደገፋችሁኝ ሁሉ ልባዊ ምሰጋናየን አቀርባለሁ::
ለቡድኑም መልካው የውድድር ጊዜን እመኛለሁ::”

ያጋሩ